1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮፓን የመታው ብርድና በረዶ ያስከተለው ችግር

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2003

አውሮፓን ከብዙ ዕንቅስቃሴዎች የገታው በቅርብ ዓመታት ታሪክ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት በረዶ ከቅዳሜ አንስቶ በመጠኑም ቢሆን ጋብ ብሏል ። ይሁን እንጂ የተቆለለው በረዶ እና ኃይለኛው ንፋስ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ አልቀረም ።

https://p.dw.com/p/QkTK
እዚህ ጀርመን አንዲት ሴት የዛፍ ቅርንጫፍ ወድቆባቸው ህይወታቸው በማለፉ ፖሊስ ዝህቡ በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀስ እየመከረ ነው ። የተከመረው በረዶ የህንፃዎችንና የመኖሪያ ቤቶችን ጣሪያዎች ደርምሷል ። በአብዛኛዎቹ አገራት የሚጥለው በረዶ እና ብርዱ ለዓመታት አጋጥሞ የማያውቅ ነው ። የአየር ፀባይ ተንባዮች እንደተናገሩት ለምሳሌ የዘንድሮው የብሪታኒያ ክረምት አገሪቱ ከ አንድ መቶ አመት ወዲህ አይታው የማታውቀው ነው ። እንደ ሌሌቹ አገራት ሁሉ ብርዱ እና በረዶው ልዩ ልዩ ዕንቅስቃሴዎችን በገታበት በብሪታኒያ በገና በዓል የተለመደው በለንደኑ Hyde park ውስጥ የሚካሄደው የማይቀረው የዋና ውድድር ውሀ በረዶ በመሆኑ ምክንያት ዘንድሮ አልተካሄደም ። ይልማ ኃሚካኤል ከበርሊን ብርዱ እና በረዶው በጀርመንና በሌሎችም የአውሮፓ አገራት ያስከተለውን ችግር ያስቃኘናል ። ይልማ ኃሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሀመድ