1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮፓውያንና የአፍሪቃ ስደተኞች

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 4 2003

በሰሜን አፍሪቃ በተቀጣጠለው ህዝባዊ አመፅ መንስኤ ወደ አውሮፓ የሚጎርፉት ስደተኞች ጉዳይ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትን ማነታረኩን ቀጥሏል ።

https://p.dw.com/p/RHOt
ምስል picture alliance/dpa
የስደተኞቹ መድረሻ የሆነችው ኢጣልያ አመፅና ጦርነት ካመሰቃቀላቸው አገራት በጀልባ የሚጎርፉ ስደተኞች ቁጥር ከአቅሜ በላይ ሆኗል ስትል ማማረር ከጀመረች ቆየች ። ኢጣልያ ችግሩን መቋቋም እንድትችል የጎረቤት ሀገራትን እርዳታ ብትማፀንም ጥያቄዋ እስካሁን ተቀባይነት አላገኘም ። የእርዳታ ያለህ ስትል የቆየችው ኢጣልያ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የቱኒዝያ ስደተኞች የ 6 ወር ጊዜያዊ የመቆያ ፈቃድ እስጣለሁ ማለቷ ሲያወዛግብ ከርሟል ። ትናንት በጉዳዩ ላይ የመከሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለይ ኢጣልያ መፍትሄ ባለችው እና ተግባራዊ ማድረግ በጀመረችው በዚህ እርምጃ ሳይግባቡ ተለያይተዋል ። ሂሩት መለሰ