1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዛውንቷ የኪነ ጥበብ ሰው

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2003

ወ/ሮ ማርታ ነሲቡ ይባላሉ፤ የጣሊያንን ወረራ በታሪክ ብቻ ሳይሆን የታሪኩ አካል በመሆን የኖሩ ናቸው።

https://p.dw.com/p/RJgq
አዛውንቷ የኪነ ጥበብ ሰው

ወ/ሮ ማርታ በአሁኑ ሰዕት በፈረንሳይ፤ ፔርፒኛኝ በተባለች ከተማ ይኖራሉ። ሰዕሊ ገጣሚ እንዲሁም ደራሲ ናቸው። በዕድሜያቸው ካሉ አረጋውያት ለየት ያለ የኪነ ጥበብ ችሎታም አላቸው። ዛሬ የ79 አመት አረጋዊት፤ ወ/ሮ ማርታ የ 6 አመት ልጅ ሳሉ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ለቀው የወጡት። አብዛኛው እድሜያቸውን በውጭው አለም ነው ያሳለፉት።

መፅሀፍ ከመፃፍ ሌላ ሰዕሊና ገጣሚ ናቸው፤ ስለ ስዕል አጥንተዋል። የተለያዩ ስዕሎችን ስለዋል። እነሱንም ለዕይታ አብቅተዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን በኮምቲውተር በመታገዝ የሚሳሉ ስዕሎችን ስለዋል።የግል ድረ ገዛቸው ላይ ሊመለከቷቸው ይችላሉ።

እንዲሁም ስለ ህይወት ታሪካቸውና የወደፊት እቅዳቸው፤ ከልደት አበበ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ያድምጡት!

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ