1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አይሮፕላን የሰራው አስመላሽ ዘፈሩ

ዓርብ፣ ሰኔ 5 2007

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳ ከልጅነቱ ጀምሮ አይሮፕላን የማብረር ህልም ነበረው። ይህ ህልሙም እቤቱ አይሮፕላን እስከመስራት አድርሶታል።

https://p.dw.com/p/1Fftf
Äthiopien Asmelash Zeferu Flugzeugbauer EINSCHRÄNKUNG
ምስል Asmelash Zeferu

አስመላሽ ዘፈሩ። ይህንን ስም በተለይ ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ገፆች አንብባችሁ ይሆናል። የሰንዳፋ ነዋሪ የሆነው አስመላሽ ዘረሩ ትንሽ አይሮፕላን ከመስራት አልፎ ትናንት ሐሙስ የመጀመሪያ የሙከራ በረራ አድርጓል።

በግሉ እና በትርፍ ጊዜው ትንሽ አይሮፕላን የሰራው የ 35 ዓመቱ አስመላሽ የጤና መኮንን ባለሙያ ነው። ይህንን ስልጠና በአለማያ ዩንቨርስቲ ከማግኘቱ በፊት ደግሞ ባይጨርሰውም ለሁለት ዓመት ተኩል በሐዋሳ ዩንቨርስቲ የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበር።

Äthiopien Asmelash Zeferu Flugzeugbauer EINSCHRÄNKUNG
ምስል Asmelash Zeferu

አስመላሽ አይሮፕላኑን ለመስራት 570 ቀናት ወይም 1 ዓመት ከ 7 ወር ገደማ ፈጅቶበታል። « አይሮፕላኗ፤ እስከ 10 000 ጫማ ከፍ ብላ መብረር እንድትችል አድርጌ ነው የሰራኃት» ይላል አስመላሽ። ትናንት ሐሙስ ምሳ ሰዓት ገደማ ለሙከራ በረራው በዝግጅት ላይ እንዳለ፤ ከበረራው ምን እንደሚጠብቅ ጠይቀነዋል፤ ከሙከራውም በኋላ አነጋግረንዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ወደ ሰንዳፋ ያቀናችው የአስመላሽ ታናሽ እህት መብራት ዘፈሩን እና ፍቅረኛው ሰብለ በቀለንም አነጋግረናል።

ሁለት ሰውን አሳፍራ ልትበር የምትችል አይሮፕላን ሰርቶ፤ ትናንት ሐሙስ ዕለት የመጀመሪያ በረራውን የሞከረው አስመላሽ ዘፈሩ ከዶይቸ ቬለ ጋር ያደረገውን ቆይታ ፤ ከዚህ በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ