አይ.ሲ.ሲ እና አፍሪቃ
ዓርብ፣ ጥር 19 2009ማስታወቂያ
28 ተኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል ። ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው ትኩረት ሰጥቶ ከሚነጋገርባቸው ውስጥ ሞሮኮ እንደገና የህብረቱ አባል ትሁን አትሁን የሚለው አወዛጋቢ ጉዳይ አንዱ ነው ። የተቋረጠው የደቡብ ሱዳን የሰላም ጥረትም ከዋነኛ የመወያያ አጀንዳዎቹ ውስጥ ተካቷል ። 54ቱ የህብረቱ አባል ሀገራት በሚቀጥለው ሳምንት ጉባኤያቸው ለህብረቱ ኮሚሽን አዲስ ሊቀመንበርም ይመርጣሉ ። ከመሪዎቹ ጉባኤዎች አስቀድሞ የሚካሄደው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባም እየተገባደደ ነው ። ከዚሁ ስብሰባ ጎን ለጎን ሰሞኑን አፍሪቃን በተመለከቱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ውይይቶች ተካሂደዋል ። ከመካከላቸው ዓለም ዓቀፉን የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አይ ሲሲን እና አፍሪቃ የተመለከተው ስብሰባ ይገኝበታል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ አለው ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ