አዲሱ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና በውጭ የሚኖሩ ሶማሊያውያን አስተያየት
ማክሰኞ፣ የካቲት 10 2001ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኦማር ሻርማርኬ ሰሞኑን ይፋ እንዳደረጉት ብጥብጥና ሁከትን ከሶማሊያ ለማስወገድ ከአክራሪዎች ጋር መወያየት ይፈልጋሉ ። የአርባ ስምንት ዓመቱ ጎልማሳ ኦማር ሻርማርኬ የትምህርት ደረጃ እና ልምዳቸው እንዲሁም ከሀገሪቱ ውጭ መቆየታቸው ለተሾሙበት ሀላፊነት ብቁ እንደሚያደርጋቸው አሜሪካን የሚኖሩ ሶማሊያውያን ለዶይቼቬለ ተናግረዋል ። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ያቀርብልናል ።