አዲሱ የሶርያ የሰላም ድርድር በዠኔቭ6 መጋቢት 2008ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2008የሶርያ ተቀናቃኝ ወገኖች አምስት ዓመት የሆነውን የሀገራቸው የርስበርስ ጦርነት ለማብቃት የሚቻልበትን መፍትሔ ለማፈላልግ ከትናንት ጀምሮ በዠኔቭ ስዊትዘርላንድ እንደገና በመካሄድ ላይ ባለው አዲስ የሰላም ድርድር ተሳትፏቸውን እንደቀጠሉ ነው።https://p.dw.com/p/1IDUMየተመድ ልዩ የሶርያ ልዑክ ስታፈን ደ ሚስቱራምስል Reuters/R. Sprichማስታወቂያ በተመድ ልዩ የሶርያ ልዑክ ስታፈን ደ ሚስቱራ መሪነት የሚካሄደው ዤኔቭ ሶስት የተባለው ድርድር በሶርያ የሽግግር መንግሥት ስለሚቋቋምበት፣ አዲስ ሕገ መንግሥት ስለሚረቀቅበት፣ እንዲሁም ፣ በቀጣዮቹ 18 ወራት ውስጥ ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫዎች ስለሚደረጉበት ጉዳዮች ይመክራል። ገበያው ንጉሤ አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ