አዲሱ የኢጣልያ ጠ/ሚኒስትር የአዉሮጳ ጉብኝት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 23 2005ማስታወቂያ
ኤንሪኮ ሌታ ትናንት አመሻሹ ላይ ጀርመን በርሊን ከመራኂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ተገናኝተዉ በአዉሮጳ ኅብረት ሀገርት ዉስጥ ያለዉን የኢኮኖሚ ቀዉስ በጋራ ትብብር እንሚወጡት ተናግረዉ በተለይ አዉሮጳ ስኬት የሚኖራት የጣልያን እና የጀርመን ግንኙነት ሲጎለብት መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይ ዛሪ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት አዲሱ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ኤንሬኮ ሌታ ሀገራቸዉ ከሚታየዉ ከፍተኛ የሥራ አጥነት፤ ከፍተኛ ዕዳ ቀዉስ እንዲሁም ባጠቃላይ ካለችበት የኢኮኖሚ ድቀት፤ ለመዉጣት ምን ዓይነት የማሻሻያ መረሃ-ግብር ይዘዉ ይሆን? በብራሰልስ የሚገኘዉን ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን ጠይቄዉ ነበር።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ