1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የዶይቼ ቬለ የመገናኛ መዋቅር

ዓርብ፣ ጥር 25 2004

የዶይቼ ቬለ የመገናኛ ብዙሃን የድረ-ገጽ አገልግሎት በተሰኘዉ አዲሱ የኢንተርኔት አድራሻ በአዲስ ንድፍ ከቴሌቭዥን መረሃ-ግብር ጋር በመጣመር ከመጭዉ ሰኞ ጥር 24 /2004 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ የድረ-ገጽ መድረኮች ይፋ ይሆናል። ስለ አዲሱ የዶቼ ቬለ ድረ ገጽ አስተያየት እንቀበላለን!

https://p.dw.com/p/13vrz

አዲሱ የዶይቼ ቬለ ድረ-ገጽ የሚያቀርባቸዉ ዘገባዎች በማህደር የተካተቱ ሲሆን፣ በጽሑፍ፤ በተንቀሳቃሽ ምስል፤ በድምጽ እንዲሁም ሁሉንም ያዛመደ አገልግሎት ይሰጣል። አዲሱ የዶይቼ ቬለ ድረ-ገጽ አድራሻ dw.de ከጀርመን ተዓማኒ መረጃዎችን ሚዛኑን በጠበቀ የጋዜጠኝነት ሞያ በሠላሳ የተለያዩ ቋንቋዎች ያቀርባል። የዶይቼ ቬለ ራድዮ ዋና አስተዳዳሪ፣ ኤሪክ በተርማን ድረ-ገጹ፣ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ በልዩ ንድፍና ደማቅ ህብረ ቀለም ስለመዘጋጀቱ እንዲህ ይገልጻሉ።

Erik Bettermann
ምስል DW

«ለኔ ይህ በየቦታዉ የምንቀርብበት የተሃድሶ ሂደት ሙከራችን ነዉ። ተሳክቶልናል ብለንም ተስፋ እናደርጋለን። በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ልዩነታችንን ይዘን አገራትን የሚመለከቱ ርዕሶቻችንን ለኅብረተሰብ ማድረስ ነዉ»

ጀርመን ዉስጥ በተሰለፈበት ሞያ የተካነዉ ዶይቼ ቬለ ጠቃሚ ድርጊቶችን እና ሂደቶችን ፈር በማስያዝ ግንኙነታቸዉን በማብራራት እና በመገምገም ሥራዉን ያቀርባል። በዚህም አዲሱ የዶቼ ቬለ ድረ-ገጽ ሁሉንም የመገናኛ ብዙሃን ዓይነት ያካትታል።

በአዲሱ ድረ ገጽ ይዘቶቹ በአርዕስት የሚመሩ እና ተገልጋዮቹ እንደሚጠብቁት በዛዉ መስመር ሁሉንም አምዶች እና ገጾች በያዘ መልኩ የተስተካከሉ ናቸዉ። ገጹ ለስዕል እና ለተንቀሳቃሽ ስዕሎች ሰፊ ቦታ፤ እና በቀን ለሚከሰቱ ዜናዎች በተለያዩ ቋንቋዎች ዝርዝር ዘገባ ያዘለ መረጃን ይዞ ይገኛል።

«አዲሱ የዶቸ ቬለ ድረ ገጽ አወቃቀር ሳቢ፤ ግልጽ፤ ቁም ነገር አዘል በመሆኑ ብዙዎች ጀመናዉያን ጥራት ባለዉ ስራ ከሚለዪበት ስራ ጋር ያመሳስሉታል። የምናሰራጫቸዉ ፕሮግራሞች በተደጋጋሚ እንደምንሰማዉ ተዓማኒነት ያለዉ የጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ያሟሉ ናቸዉ። በቋንቋም ደረጃዉን የጠበቀ፤ በቀለም ያሸበረቀ ሆኖ ነዉ የቀረበ ነዉ»

የዶይቼ ቬለ የመገናኛ ዘዴዎች ማዕከል ማህደር በቀጥታ ወድያዉኑ በ dw.de ድረ-ገጽ ተቆራኝቶ የሚቀርብ ነዉ። በመሆኑን ተጠቃሚዎች በቀጥታ ተንቀሳቃሽ ስዕሎች ድምጾች እና ፎቶግራፎች፤ እንዲሁም ከተለያየዉ የዶይቼ ቬለ የዘገባ ማህደር የተሰራጩ ዝግጅቶች በተራ ከሚቀርቡ ርኦለ ጉዳዮች ጋር ማግኘት ይችላሉ።

የዶይቼ ቬሌ ቴሌቭዥንም በአዲስ የማሰራጫ መስመሮች ዝግጅቶቹን በአዲስ አቅድ ያቀርባል። የቴሌብዥን መረሃ-ግብሩ እስከ አሁን ቀደሙ ሁሉ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎችን በተከታታይ ያሰራጫል። በተጨማሪም የዜና መጽሄት፤ ዘገባዎችን እና የተሰናዱ ዘጋቢ ፊልሞችን በተለያዩ አርዕስት መረጃዎችን ያቀርባል።

Deutsche Welle Relaunch Startseite Deutsch
ምስል DW

በዶይቼ ቬሌ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የራድዮዉ እና የቴሌቭዝን ጣብያዉ ጥምር የሙዚቃ አጠቃቀምን ፈጥሯል። ይህም ራድዮና የቴሌቭዥን አገልግሎቱ በጥምር በመሥራት አዲስ ንድፍን ቀይሰዋል። አይዲ የተሰኘዉ መደብ ከቴሌቭዥን ዝግጅት ድምፆች ወደ ራድዮ እና ቴሌቪዥን የሚያሠራጭበት ይሆናል» ይህ ማለት የድምጽ ንድፍን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በመቀያየር ማሠራጨት ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ