1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የጀርመን ፕሬዝዳንት ክርስቲያን ቩልፍ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 29 2002

አዲሱ የጀርመን ፕሬዝዳንት ክርስቲያን ቩልፍ ጀርመን ውስጥ በሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል መገናኛ ድልድይ የመፍጠርንና ጀርመን የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን ይበልጡን ከህብረተሰቡ ጋር የማዋሀድን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/OC4w
ምስል AP

« የጀርመን ህዝብን ደህንነትና ጥቅምን ለማስጠበቅ ፣ ሊደርስባቸው ከሚችል አደጋ ለመከላከል ፣ የሀገሪቱን ህገ መንግስትና የፌደራሉን ህጎች ለማስከበር የአቅሜን ሁሉ እጥራለሁ ። ሀላፊነቴን በትክክል እና በተገቢው መንገድ ለመወጣት ፣ ፍትህ ለሁሉም እኩል እንዲደርስ ለማድረግ እንደምጥር ቃል እገባለሁ ። ለዚህ ስኬት ፈጣሪ ይርዳኝ »
አዲሱ የጀርመን ፕሬዝዳንት ክርስቲያን ቩልፍ ባለፈው ሳምንት አርብ በመረጡዋቸው በጀርመን የህዝብ ዕንደራሴዎች ምክር ቤት ቡንደስታህ አባላትና በ 16 ቱ ፌደራል ክፍላተ ሀገር ተወካዮች ፊት የፈጸሙት ቃለ መሀላ ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ