1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የፈረንሳይ የአሰሪዎች ህግና የውጭ ዜጎች ተቃውሞ

ረቡዕ፣ መጋቢት 29 2002

ፈረንሳይ ውስጥ በተወሰኑ የስራ መስኮች የተሰማሩ ሰራተኞች በተለይም መንግስት ህገ ወጥ የሚላቸው የውጭ ዜጎች ከወራት አንስቶ አድማ ላይ ናቸው ። በተቃውሞው የተካፈሉ ወገኖች ጥያቄ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ይሰጠን የሚል ነው ።

https://p.dw.com/p/MoYv
ኒኮላ ሳርኮዚምስል AP
መንግስት በበኩሉ ህገ ወጥ የሚላቸውን ሰራተኞች በሚቀጥሩ አሰሪዎች ላይ ጠበቅ ላይ ህግ ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል ። በዚህ ህግ መውጣት ቁጥራቸው ወደ አራት መቶ ሺህ የሚጠጋ ፈረንሳይ የሚገኙ ህገ ወጥ ሰራተኞች ችግር ላይ ይወድቃሉ የሚል ስጋት አለ ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። አብረን እንቆይ ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሀመድ