አዲስ አበባ ለኢትዮጵያውያን ንቅናቄ
ሰኞ፣ መጋቢት 9 2011ማስታወቂያ
«አዲስ አበባን እና ሰማይን የኔ ነው» የሚልን አንቀበልም ሲል አዲስ አበባ ለኢትዮጵያዊያን ንቅናቄ ለ«DW» ተናገረ፡፡ ምንም አይነት የፖለቲካ ፍላጎት እንደሌለው የሚናገረው በቅርቡ የተቋቋመው ይኽው ንቅናቄ አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያዊያን እና የአፍሪቃ መዲና መሆኗን ስለምናምን ለሁለንተናዊ እድገቷ እና ለህዝቦቿ ጥቅም እንጮሃለን ብሏል፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ነች የሚለው ንቅናቄው በመላው ዓለም የሃሳቡ ተጋሪ ከሆኑት ጋር በጉዳዩ ላይ ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታውቋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ