1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባ፣ ወንጀለኞች መያዛቸው

ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2011

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባለፈዉ ሳምንት ቅዳሜ ለሁለት ሰዓታት ባደረገዉ ፍተሻ ብቻ ከ200 በላይ ሕገ-ወጥ አሽከርካሪዎች መያዙን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3IUsu
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

ቃለ ምልልስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋር

 የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በተለይ ለዶቸ ቬለ DW በስልክ እንደነገሩት ፍተሻዉ ከ10 እስከ 12 ሰዓታት በነበረዉ ጊዜ በአምስት ክፍለ-ከተሞች ድንገት የተደረገ ነበር።  በፍተሻዉ ሕገ-ወጥ መድሐኒቶች፤ ሞተር ብስኪሌቶችን ይዟል።ፖሊስ ቀዳሜዉኑ ሌሊቱን ቦሌ ክፍለ-ከተማ በሚገኙ የራቁት ጭፍራ ቤቶች ባደረገዉ አሰሳ አደገኛ ዕፅ፣ ለአደገኛ ዕፅ ሽፋን የሆኑ የሺሻ ማጤሲያዎች፣ አንድ ሽጉጥና 8 ተጠርጣሪ ሰዎችን ይዟል። ኮማንደር ፋሲካ፣ ፖሊስ ከዚሕ ቀደም ባደረገዉ አሰሳና ቁጥጥር የጦር መሳሪዎችንና የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን መያዙን አስታዉሰዋል።ኮማንደር ፋሲካን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል። 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ