1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ውሎ

ዓርብ፣ ሰኔ 26 2012

በከተማዋ አውቶብሶች ታክሲዎች የቀድሞ አገልግሎታቸውን እንደቀጠሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችም እየተካሄዱ መሆኑን በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎችም ተዘዋውሮ መመልከቱን ስየአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዘግቧል።በሌላ በኩል የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር ወይዘሮ አስቴር ስዩም መታሰራቸውን ባለቤታቸውና ፓርቲያቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3elBM
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist

የአዲስ አበባ የዛሬ ውሎ

ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ እንቅስቃሴዋ ተግቶ የነበረው አዲስ አበባ ዛሬ ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ ተመልሳለች ይለናል የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ። በከተማዋ አውቶብሶች እና ታክሲዎች የቀድሞ አገልግሎታቸውን እንደቀጠሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችም እየተካሄዱ መሆኑን በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎችም ተዘዋውሮ መመልከቱንም ተናግሯል።በሌላ በኩል የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር ወይዘሮ አስቴር ስዩም መታሰራቸውን ባለቤታቸውና ፓርቲያቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡት የፓርቲው መሪ አቶ እስክንድር ነጋ ደግሞ የጊዜ ቀጠሮ ተስጥቶላቸዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ