1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባ ውስጥ የትራንስፎርመሮች መሠረቅ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2011

በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ እና ቦታ በአንድ ወር ውስጥ 7 የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮች መሰረቃቸውን የከተማው ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለ ዶይቼ ቬለ «DW» አረጋገጠ። ከተሰረቁት ትራንስፎርመሮች መካከል አምስቱ እስካሁን የደረሱበት አለመታወቁን እና ወንጀለኞችም አለመያዛቸውንም በአገልግሎቱ የኮሙኑኬሽን ሥራ አስኪያጁ አቶ በቀለ ክፍሌ ተናግዋል።

https://p.dw.com/p/3Lw8D
Äthiopien | Elektrizitätswerkswerke Addis Abeba
ምስል DW/S. Muche

ትራንስፎርመሮቹ የተሰረቁት ከሦስት የተለያዩ ሰፈሮች ነዉ

በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ እና ቦታ በአንድ ወር ውስጥ 7 የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮች መሰረቃቸውን የከተማው ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለ ዶይቼ ቬለ «DW» አረጋገጠ። ዕቃዎቹ በሦስት የተለያዩ አካባቢዎች የተዘረፉ ሲሆን ከዚህም መካከል ከባድ የዕቃ መጫኛና ማውረጃ ተሽከርካሪ ተጠቅመው አገልግሎት ይሰጥ የነበረን ትራንስፎርመር ሲያወርዱ እጅ ከፈንጅ የተያዙ ይገኙበታል። ከተሰረቁት ትራንስፎርመሮች መካከል አምስቱ እስካሁን የደረሱበት አለመታወቁን እና ወንጀለኞችም አለመያዛቸውንም በአገልግሎቱ የኮሙኑኬሽን ሥራ አስኪያጁ አቶ በቀለ ክፍሌ ተናግዋል። በመሥሪያ ቤቱ የኤሌትሬክ ገመድ ቆረጣ እና ስርቆት እንጅ እንዲህ ያለው ድርጊት አጋጥሟቸው እንደማያውቅ ጠቅሰው ፣ ክስተቱ ግን በተጠናና የዕቃውን ሁኔታና ጥቅም ብሎም ውስጡን በሚያውቅ አካል ሳይፈጸም እንዳልቀረ ግምታቸውን ተናግረዋል። በተቋሙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ትራንስፎርመሮች በብልሽት ተቀምጠው እንደሚገኙም ተናግረዋል።


ሰለሞን ሙጬ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ