1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ የፍልሰት ፖሊሲ ለአፍሪቃ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 10 2009

በባህር በኩል እያደረጉ ወደ አውሮጳ ለመግባት ከሚሞክሩ ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ አፍሪቃውያን ናቸው። ይሁንና፣ በገሀድ እንደሚታየዉ፤ ከአፍሪቃውያን ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ አሁንም በዚያው በአፍሪቃ ከአገራቸው እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ናቸው።

https://p.dw.com/p/2UYdV
Italien gerettete Bootsflüchtlinge im Hafen von Catania
ምስል Reuters/A. Parrinello

Richtungswechsel: Afrika braucht eine neue Migrationspolitik - MP3-Stereo

 በአፍሪቃ  በሕዝብ ቁጥር ጭማሪ የተነሳ ወደፊትም የስደተኞች እና የፍልሰት ጫና ከፍተኛ እንደሚሆን ነው የሚገመተው። ይህን ለመታገል ምን ዓይነት ስልት ማውጣት ያስፈልጋል?  የአውሮጳ ኅብረት ከአፍሪቃውያት ሃገራት ጋር በደረሱት የፍልሰት ስምምነት፣  የተገን ማመልከቻቸው ተቀባይነት ያላገኙት ስደተኞችን መልሰው በመቀበሉ ጉዳይ ጭምር የመጀመሪያ ግምገማ አድርገዋል።

ሰዎችን ለስደት ከሚዳርጉት ምክንያቶች መካከል ጦርነት እና ረሀብ ዋነኞቹ  ናቸው።  በሰሜን ናይጀሪያ ለምሳሌ አሸባሪው ቡድን ቦኮ ሀራም ባስፋፋው ሽብር ሰበብ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወደ አውሮጳ፣ ሁለት ሚልዮን የሚሆኑ ደግሞ በሀገራቸው ተፈናቅለዋል።  የአፍሪቃን ያህል ስደተኞችን የሚያስተናግድ አህጉር የለም። በተመ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት ዘገባ መሠረት፣ 15 ሚልዮን ስደተኞች ይገኛሉ። ስደተኞቹ አዘውትረው ከለላ የሚያገኙት ድሆች በሆኑት ጎረቤት ሃገራት ነው። ይህም በመጀመሪያ ደረጃ በአስተናጋጆቹ ሃገራት ላይ ትልቅ ችግር በማስከተል በዚያ የሚታየውን ድህነት ይበልጡን አስከፊ ያደርገዋል፣ በሁለተኛ ደረጃም ፍልሰትን ያጠናክራል። በዚህም የተነሳ፣  በአህጉሩ ስደተኞችን ተቀብለው የሚያስተናግዱት ሃገራት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያስ ሊቀርብላቸው እንደሚያስፈልግ የተመ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አሳስበዋል። 
« ይህ ዓለም አቀፍ ቀውስ ነው። ስለዚህ አጠቃላይ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል። ስደትን አስቀድሞ መከላከል፣ ስደተኞች አስተናጋጅ ሃገራትን ማገዝ፣ አማራጭ የፍልሰት መንገድ ማዘጋጀት፣ እንዲሁም፣ ተገን የማግኘት መብትን ማጠናከር የተሰኙትን አራት ርምጃዎች እኩል በተግባር መተርጎም አስፈላጊ ይሆናል። »
በአፍሪቃ የሕዝብ ቁጥር ፈጥኖ በማደግ ላይ የሚገኝበት እውነታም ሌላው የስደት ምክንያት መሆኑ ይነገራል።  ሰዎች ሀገራቸውን ለቀው እንዳይወጡ ከተፈለገ ፣ ሕይወታቸውን መምራት የሚችሉበት አስተማማኝ ሁኔታ ፣ ማለትም፣  የሥራ ቦታሊፈጠርላቸው ይገባል፣ በሚገባ የሚሠራ መሠረተ ልማትም ያስፈልጋቸዋል። እዚህ ላይ   የአውሮጳ ኅብረት ገበያዎቹን በመዝጋት ፈንታ፣ የአፍሪቃ ሃገራትን ጭምር ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንግድ ውሎችን በማዘጋጀት እና እስከዛሬ በሚከተለው የፍልሰት ፖሊሲ ላይ ለውጥ በማድረግ  ሊረዳ  እንደሚችል የፍልሰት እና የምጣኔ ሀብት ጠበብት ጠቁመዋል።

UNHCR Filippo Grandi
ምስል picture alliance/AP Photo/S. Di Nolfi

ዳግማር ሲንደ/አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ