1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ችግሮች

እሑድ፣ መጋቢት 16 2010

በመፍትሄነት የሚቀርቡት ሃሳቦችም፣ ተሀድሶ፣ ሁሉን አሳታፊ ውይይት፣ አዲስ ምርጫ አገራዊ መግባባት ከሚሉት አንስቶ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግሥት መመስረት እስከሚሉት ይደርሳሉ።

https://p.dw.com/p/2utB5
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ውይይት፦ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሄ ይሆን?

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውሶች እንዴት ይፈታሉ ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ ወገኖች የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዝራሉ። በመፍትሄነት የሚቀርቡት ሃሳቦችም፣ ተሀድሶ፣ ሁሉን አሳታፊ ውይይት፣ አዲስ ምርጫ አገራዊ መግባባት ከሚሉት አንስቶ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግሥት መመስረት እስከሚሉት ይደርሳሉ። እነዚህ ሃሳቦች ቀደም ካሉት ጊዜያት አንስቶ ይንሸራሸሩ የነበረ ቢሆንም ተደጋግመው መሰማት የጀመሩት ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ካሳወቁ እና አለመረጋጋቱ ከቀጠለ በኋላ ነው። ከኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የ9ቀናት ዝግ ስብሰባ በኋላ በዚህ ሳምንት የተካሄደው የፓርቲው ምክር ቤት ስብሰባ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትርን እና የገዥውን ፓርቲ ሊቀመንበር መርጧል ወይም ይመርጣል ። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት አለማምጣቱ አሁንም ማነጋገሩ ቀጥሏል። የዛሬው እንወያይ በዚህ ላይ ያተኩራል። በውይይቱ የሚሳተፉት ዶክተር መሐሪ ራዳኤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ክቡር ገና ኢኒሽየቲቭ አፍሪቃ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሃላፊ  እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም መቀመጫውን ብራሰልስ ያደረገው ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ማህበር  ሃላፊ ናቸው። ውይይቱን ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

ኂሩት መለሰ