1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ፕሬዝደንት በሶማሊያ፤ የአፍሪቃው ቀንድ የፖለቲካ ይዞታ

እሑድ፣ ግንቦት 21 2014

ለሦስት አስርት ዓመታት በግጭት ጦርነት በምትታመሰው የአፍሪቃው ቀንድ ሀገር ሶማሊያ ፕሬዝደንቱ የሚመረጡት በምክር ቤት አባላት ድምጽ ነው። የምክር ቤት አባላቱ ደግሞ በጎሳ መሪዎች ይሰየማሉ።

https://p.dw.com/p/4By9H
Äthiopiens Premierminister Abiy Ahmed, Eritreas Präsident Isaias Afwerki und Somalias Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

እንወያይ

ሶማሊያ አዲስ መሪዋን መርጣለች። ከአንድ ዓመት በላይ ሲያወዛገቡ የከረሙት የሶማሊያ ፖለቲከኞች ከዚህ ቀደም ሥልጣኑን ይዘው የነበሩትን ሀሰን ሼኽ መሀሙድን ለሁለተኛ ጊዜ በፕሬዝደንነት ሰይመዋል። ከአጎራባች ሃገራት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች ጋር እጅግ የተቀራረበ ወዳጅነት ፈጥረው የነበሩት የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝደንት መሀመድ አብዱላሂ አካሄድ በተለይ ለምዕራባውያን ሃገራት እንዳልጣመ የሚናገሩ ወገኖች አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝደንት በአፍሪቃው ቀንድ ሊከተሉት የሚችሉት አዲስ ፖሊሲ ሊኖር እንደሚችል ይገምታሉ። በሌላ ወገን የለም የትኛው የሶማሊያ ፕሬዝደንት ለሀገሪቱ መረጋጋትም ሆነ ለቀጣናው ሰላም የሚበጀውን ለማድረግ ከመሞከር ወደኋላ አይልም ባይ ናቸው። በዚህም የአስመራ አዲስ አበባ መቃዲሹ ትስስር ቀጣይነት አማራጭ እንደሌለውም ያመላክታሉ። በዓለም ፖለቲካ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የአፍሪቃው ቀንድ የፖለቲካ እና የጸጥታ ይዞታ ወዴት ያመራል? የሰላም አቀንቃኝ የሚባሉት ሀሰን ሼኽ ማህሙድስ ሀገራቸውንም ሆነ አካባቢውን የማረጋጋት አቅም ይኖራቸው ይኾን? በሚል ዶቼ ቬለ ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ