1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዳጊዎቹ ሀገሮችና ቱሪዝም

ረቡዕ፣ መስከረም 17 1999

ለጥቂት ጊዜ በፊት ቀንሶ የነበረው ወደ እሥያ፡ አፍሪቃ፡ወደ ላቲን አሜሪካ---->

https://p.dw.com/p/E0dT
ቱሪስቶች በሊባኖስ
ቱሪስቶች በሊባኖስምስል picture-alliance/dpa

ወይም ካሪቢክ የሚጓዘው ሀገር ጎብኚ ቁጥር እንደገና እየጨመረ መሄዱን እዚህ ጀርመን ሀገር የወጣ አንድ ጥናት አስታወቀ። ሽታርንቤርገር የተሰኘው የቱሪዝምና ልማት ክበብ ባወጣው ጥናት መሠረት፡ እአአ በ 2005 ዓም ለዕረፍት ከወጡት ጀርመናውያን መካከል ሰባት ነጥብ ሰባቱ ሚልዮን ወደ አዳጊዎቹ ሀገሮጭ ተጉዘዋል። ይህም እአአ በ 1991 ዓም ከነበረው በዘጠኝ ከመቶ ከፍ ብሎ ነው የተገኘው። የዓለም ቱሪስት ድርጅት ዘገባ እንዳመለከተውም፡ አዳጊዎቹን ሀገሮች የጎበኘው ቱሪስት ቁጥር ሠላሣ ስድስት ከመቶ ነው። ይሁንና፡ ድሆቹ የአዳጊዎቹ ሀገሮች ሕዝቦች ከዚህ የቱሪስቶች ጉዞ ከሚያስገኘው ገንዘብ ተጠቃሚዎች አልሆኑም።