1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አድማና ተቃዉሞ በህንድ

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2005

ዛሬ በበርካታ የህንድ ከተሞች ሱቆችና መስሪያ ቤቶች ተዘግተዉ፤ የህዝብ መጓጓዣ ስልቶችም ተስተጓጉለዉ ዉለዋል።

https://p.dw.com/p/16C5n
ምስል AFP/Getty Images

ለሀገር ዓቀፍ አድማዉ መንስኤ የሆነዉ መንግስት የዉጭ ባለወረቶች በሀገሪቱ የችርቻሮ መደብሮች ላይም ገንዘባቸዉን እንዲያዉሉ መፍቀዱ ሲሆን የነዳጅ ዋጋ መናርም ሌላዉ ምክንያት ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቱና የዋጋ ጭማሪዉን ይፋ ያደረገዉ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሀን ሲንግ ፓርቲ በምህፃሩ UAP፤ ርምጃዉን የወሰደዉ የሚንገዳገደዉን የሀገሪቱን ኤኬኖሚ ለመደገፍ እንደሆነ አመልክቷል።

Manmohan Singh
ምስል AFP/Getty Images

ርምጃዉ ግን መላ ሀገሪቱን ያዳረሰ ተቃዉሞ አስከትሏል። ከዚህም ሌላ የፓርቲዉ ተጣማሪና ደጋፊ የሆነዉ የትሪናሞል ምክር ቤትም ለሲንግ መንግስት የሚሰጠዉን ድጋፍ እንደሚያቆም አስጠንቅቋል። ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ከተዘጉት የንግድ ቤቶችና መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ ጎዳና ላይ በወጡ ተቃዋሚዎች መንገዶች መዘጋታቸዉና የትራፊክ እንቅስቃሴዉ መስተጓጎሎ ተገልጿል። የሀገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ተቃዋሚ ባህራቲያ ጃንታ ፓርቲ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የሠራተኛ ማኅበራት ጋ በመሆን ተቃዉሞዉን ማስተባበሩ ተዘግቧል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ