1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አገረ-ሰባዊ ልማድ ምልኪ

Azeb Tadesseማክሰኞ፣ ጳጉሜን 6 1999

አንድን ነገር ከማህበራዊ ክስተት ጋር በማያያዝ፣ እንዲህ ነገር ሲሆን፣ እንዲህ ይሆናል፣ ብሎ፣ ወደፊት ሊመጣ የሚችልን መጥፎ እድል፣ ወይም ጥሩ እድል፣ የመተንበያ ልማድ፣ ምልኪ ይባላል

https://p.dw.com/p/E0mA
ቶይ ቶይ ቶይ
ቶይ ቶይ ቶይምስል AP

በጀርመን እንደዉ በዘልማድ ጥቁር ድመት ሲያቋርጥ፣ የፊት መመልከቻ መስታወት ሲሰበር እና 13 ቁጥር በተለያየ መንገድ ሲያጋጥም፣ አይቀናም ገድ የለዉም! የሚል፣ አገረ ሰባዊ ልማድ አለ። በያዝነዉ በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን በኛ ወይም በታዳጊዉ አገር ብቻ ሳይሆን እንዲህ አይነት ልማድ እና እምነት ያለዉ፣ በጣም በስልጣኔ፣ በቴክኖሎጂ፣ በመጠቁ አገራትም ይህ አይነቱ አገረሰባዊ ልማድ ወይም እምነት በጉልህ ይታያል። በጀርመን በኖርድ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት፣ በህብረተሰብ ቁሳዊ ባህል ስር የአገረሰባዊ ባህል አዋቂ Dr.Alois Döring በጀርመን ያለዉ አገረሰባዊ እምነት፣ ልማድ ምን ይመስላል? ስንል ጠይቀናቸዉ፣ በአገራቸዉ ስላለዉ አንዳንድ አገረ ሰባዊ እምነት እና ልማድ አጫዉተዉናል መልካም ቆይታ።