1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አጣብቂኝ ዉስጥ የገባችዉ የግሪክና አዉሮጳ እጣ

ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2007

በከፍተኛ እዳ መዘፈቋ የሚነገረዉ ግሪክ ተጨማሪ ብድር እንድታገኝ ከፈለገች ከአበዳሪዎቿ የተጠየቀችዉን አሳማኝና ተጨባጭ የማሻሻያ እቅድ እንድታቀርብ አሁንም እየተጠየቀች ነዉ። የግሪክ

https://p.dw.com/p/1Ffqf
Griechenland - Alexis Tsipras spricht im Parlament
ምስል REUTERS/Alkis Konstantinidis

[No title]

ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ትናንት ማምሻዉን ከጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና ከፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦሎንድ ጋ ለብቻቸዉ ተነጋግረዋል። ብራስልስ ላይ በአዉሮጳና በላቲን አሜሪካን መሪዎች መካከል ከሚካሄደዉ ጉባኤ ጎን የሶስቱ መሪዎች መሪዎች ዉይይት እንደተገመተዉ ተጨባጭ ዉጤት አላስገኘም። የአዉሮጳ ኮሚሽን ግሪክ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም፤ ከአዉሮጳ ማዕከላዊ ባንክና ከአዉሮጳ ኮሚሽን የቀረበለትን የመፍትሄ ሃሳብ መቀበሉን አረጋግጦ የጠየቀዉን ብድር ማግኘት እንደሚችል ግልፅ አድርጓል። ከአዉሮጳ መሪዎቿ ጋ የሚደራደሩት ሲፕራስ የቀረበላቸዉን የቁጠባ እቅድ እንዳይቀበሉ ከአቴንስ የተቃዉሞ ግፊት አይሎባቸዋል። የግሪክን ቀዉስና የመፍትሄ ድርድሩን አስመልክቶ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን በስልክ አነጋግሬዉን ነበር። ገበያዉ ከትናንቱ ዉይይት የተገኘዉን ዉጤት በመተንተን ይጀምራል።

ገበያዉ ንጉሤን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ