1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና ብርሃን ያላረፈበት የባለሙያዎቿ ፈጠራ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 20 2003

ዓለም ዓቀፍ የጤና ባለሙያዎች በአፍሪቃ በርካታ የፈጠራ ስራዎችና ባለሙያዎቹ የምርምር ዉጤታቸዉ ይፋ ስለማይወጣ ካሉበት ከፍ አለማለታቸዉንና ለተጠቃሚዉ ኅብረተሰብም መድረስ እንዳልቻለ አመለከቱ።

https://p.dw.com/p/Ql5Z
ምስል AP

የጤና ባለሙያዎቹ ብሪታኒያ ላይ ባሳተሙት የህክምና መጽሔት ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ አገራት የሚፈጠሩትን አዳዲስ የህክምና ዉጤቶች አደባባይ አለማዉጣታቸዉ የተገኙት ዉጤቶች ተድበስብሰዉ እንዲቀሩ ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል። ስምንት የአፍሪቃ አገራት ላይ በተካሄደ ጥናት የተደገፈዉ የባለሙያዎቹ ዘገባ እንዳመለከተዉ ክፍለ ዓለም አፍሪቃ በራሷ ልጆች የፈጠራ ዉጤት ለመጠቀም ባለሙያዎቿ ድንበር ሳያግዳቸዉ በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል።

ሃና ደምሴ

ነጋሽ መሐመድ