1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና ቴክኖሎጂ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 16 2005

የቴክኖሎጂዉ እድገት የፈጠረዉ ክፍተት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ተንቀሳቃሽ ሥልክና ኢንተርነት በአንፃራዊነት በተስፋፋባቸዉም ሐገራት የሚታይ ነዉ።ናይሮቢ-ኬንያ የሚገኘዉ የጥናንት ተቋም ባልደረባ ያስፐር ግሮስኩርት እንደሚሉት ቴክኖሎጂዉ ቢኖር እንኳ አንዳዴ ዉጤቱ መጥፎ ነዉ።

https://p.dw.com/p/18MtI

በጀርመን የምጣኔ ሐብት ማሕበር የአፍሪቃ ክበብ፥ የማሌኪ ቡድን ከተሰኘዉ የመረጃ ድርጅት ጋር በተባባር ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀዉ የአፍሪቃ የንግድ ሳምንት በጀርመንዋ የንግድ ማዕከል ፍራንክፈርት ዉስጥ በመካሔድ ላይ ነዉ።ዶቸ ቨለም የመገናኛ ዘዴዎች ተባባሪ በበመሆን በትርዒቱ ከሚሳተፉ ተቋማት አንዱ ነዉ።በሚደረጉት ዉይይቶች፥ ሴሚናሮች እና ድግሶች ላይ የአፍሪቃና የጀርመን የተለያዩ ኩባንዮችና የንግድ ተቋማት ተጠሪዎች፥ ፖለቲከኞች፥ አምባሳደሮች፥ባለሐብቶችና የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች ይካፈላሉ።ዉይይት ከሚደረግባቸዉ ጉዳዮችየመረጃ ቴክኖሎጂ (IT) በእንግሊዝኛ ምሕፃረ-ቃሉ አብዮት ለአፍሪቃ የሚኖረዉ ፋይዳ አንዱ ነዉ።ማያ ብራዉን የዘገበችዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።


ለታንዛኒያዊዉ የኤሌክትሪክ ሐይል አከፋፋይ ድርጅት ሐላፊ ለፌልሽስሚ ምራምባ፥ ተንቀሳቃሽ ሥልክ ፈጣን መልዕክት መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ መሳሪያም ብቻ አይደለም።የኤሌክትሪክ ሐይል መሸጪያና መግዢያም ጭምር እንጂ።

«እዚሕ ጀርመን እንኳን ሆኜ፥ በተንቀሳቃሽ ሥልኬ ከሐገሬ የኤሌክትሪክ ሐይል መግዛት እችላለሁ።ይሕ በቴክኖሎጂዉ መስክ የታየ ተጨባጭ አብዮት ነዉ።»

የፍራንክፈርቱን ትርዒት የሚገበኙ ባለሙያዎች እንደሚስማሙበት የመረጃ ልዉዉጥ ቴክኒክ (ICT) በሐይል መስክ ይሁን በጤና፥ በትምሕርት ወይም በሥልጠና በሁሉም መስክ የሰዎችን ኑሮና እንቅስቃሴ ማሻሻሉ አላጠያየቀም።በንዳድ የአፍሪቃ ሐገራትም ከፍተኛ ለዉጥ ማምጣቱ ተረጋግጧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባኤ (UNCTAD) እንዳስታወቀዉ፥እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ከሁለት ሺሕ ጀምሮ ከኬንያ አመታዊ ገቢ አንድ-አራተኛ ያሕሉ የሚገኘዉ ከመረጃና መገናኛ ቴክኒክ ነዉ።

ይሕ ማለት ግን ሁሉም የአፍሪቃ ሐገራት ከዚሕ ደረጃ ደርሰዋል ማለት አይደለም።ማላዊ ቴክኖሎጂዉ ከነጥቅሙ ከራቃቸዉ ሐገራት አንዷ ናት።የሐገሪቱ የማስታወቂያ ሚንስትር ሞሰስ ኩንኩዩ ችግርና መፍትሔዉን ይናገራሉ።

«ትልቁ ፈተና የሐገሪቱ የምግብ ቅርጫት ለሆነዉ ለገጠሪቱ ሕዝብ ICTን ማዳረሱ ነዉ።የሚገኘዉን ጥቅም ለማሳደግ ፈጠራን ማሻሻልና ICTን ለነሱ ማዳረስ አለብን»

የቴክኖሎጂዉ እድገት የፈጠረዉ ክፍተት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ተንቀሳቃሽ ሥልክና ኢንተርነት በአንፃራዊነት በተስፋፋባቸዉም ሐገራት የሚታይ ነዉ።ናይሮቢ-ኬንያ የሚገኘዉ የጥናንት ተቋም ባልደረባ ያስፐር ግሮስኩርት እንደሚሉት ቴክኖሎጂዉ ቢኖር እንኳ አንዳዴ ዉጤቱ መጥፎ ነዉ።

«ከሚያገኙት ገንዘብ በላይ ለሥልክ ለማዉጣት የሚፍጨረጨሩ አንዳድ ሰዎች አሉ።በቀን ሥራ ከሚያገኙት ገቢ የተሻለ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ሌላዉን ሥራ ትተዉ ጥሪታቸዉን ሁሉ ሥልክና የሥልክ ካርድ ላይ ያዉላሉ።ይሕ ማለት (ከስልኩ ወይም ከኢንተርኔቱ) ላለመዉጣት ብቻ ከአቅማቸዉ በላይ ገንዘባቸዉን ያባክናሉ።»

በተንቀሳቃሽ ሥልክ ኢንተርኔትን ከሚገባዉ በላይ መጠቀም ግሮስኩርት እንደሚሉት የቴክኖሎጂዉ አብዮት ከሚሰጠዉ ጥቅም ይልቅ ተጠቃሚዉን ከወጪዉ በተጨማሪ ለችግር ያጋልጣል።መስመሩ ሊዛባ፥ ሊበላሽ ይችላል።ሲከፋ ደግሞ በተለይ አምባገነን ሥርዓት ባለባቸዉ ሐገራት የተጠቃሚዉ መረጃዎች ከሥርዓቱ እጅ ሊገባ ይችላል።

ለዚሕም ሰበብ የUNCTAD የIT ጉዳይ ተንታኝ ቶርብዮርን ፍሬድሪክሰን የቴክኖሎጂዉ መስፋፋት ከአጠቃቀም እዉቀት ጋር መቆራኘት አለበት የሚሉት።

«ያሁኑ ትኩረት መሆን ያለበት የመሠረተ ልማት አዉታሮችን ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ITCን በተገቢዉ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ክሒልንም ማዳበርን መጨመርም አለበት። በየሐገሩ ድጋፍ የሚሰጡና የቴክኖሎጂዉን አጠቃቀም የሚያስፋፉ ተቋማት ከተፈጠሩ የአፍሪቃ ሐገራትና የንግድ ተቋማት ቴክኖሎጂዉን ለየሥራቸዉ በሚያስፈልጋቸዉ መስክ እንዲያዉሉትና እንዲጠቀሙበት ማድረግ ይቻላል።»

ፍሬዲክሰን እንደሚሉት በተወሰኑ የአፍሪቃ ሐገራት አሁንም ሥማርት ፎን የሚባለዉን አይነት የተንቀሳቃሽ ሥልክ ለሚሠሩ ለኢንተርነት ገፅ አቅራቢዎች አዳዲስ ገበያ ተፈጥሯል።ኬንያ ዉስጥ የተጀመረዉ በተንቀሳቃሽ ሥ’ልክ ገንዘብ ማዘዋራር በአለም አቀፍ ደረጃ እዉቅና አግኝቶ ብዙዎች ሥራዬ ብለዉ ይዘዉታል።ይሁንና በተንቀሳቃሽ ሥልክ ገንዘብ ማስተላለፉ እስካሁን ወጥ ሕግ አልተበጀለትም።

ነጋሽ መሐመድ

Bildbeschreibung: (Alle Angaben in deutscher Schreibweise, also z. B. nicht Baghdad, sondern Bagdad, Wladimir und nicht Vladimir) Titel: Arnulf Christa und Jaiye Doherty auf der Africa Business Week Schlagworte: Africa Business Week, Afrika Wer hat das Bild gemacht?: Adrian Kriesch (DW Afrika) Wann wurde das Bild gemacht?: 21.5.2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Frankfurt Bildbeschreibung: Bei welcher Gelegenheit / in welcher Situation wurde das Bild aufgenommen? Wer oder was ist auf dem Bild zu sehen? Arnulf Christa und Jaiye Doherty auf einem Panel der Africa Business Week In welchem Zusammenhang soll das Bild/sollen die Bilder verwendet werden?: Artikel / Bildergalerie / Dossier (Nichtzutreffendes bitte löschen, u. U. genauere Angaben ergänzen) Artikel Bildrechte: (Grundsätzlich nur eine Variante möglich, Nichtzutreffendes bitte löschen.) - Der Fotograf / die Fotografin ist (freie) Mitarbeiter(in) der DW, so dass alle Rechte bereits geklärt sind.
ዉይይትምስል DW
Bildnummer 54653914 Date 14 02 2008 Copyright Imago Anka Agency International African Woman Using a cellphone PUBLICATIONxNOTxINxRSA Symbolic image Indoor Kbdig xsp 2008 horizontal o0 Africa South Africa Woman Body parts Hand Nail polish Smartphone Handy
ምስል imago

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ