1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና የምግብ ዋስትና ጉባዔ በዩጋንዳ

ረቡዕ፣ መጋቢት 22 1996

አፍሪቃን እአአ 2020 ዓም ድረስ በምግቡ ዋስትና ራስ አገዝ ማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመምከር ከሀምሳ የዓለም ሀገሮች የተውጣጡ ወደ አምስት መቶ የሚጠጉ ልዑካን በነገው ዕለት በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ የሦስት ቀናት ዓቢይ ጉባዔ ይከፍታሉ።

https://p.dw.com/p/E0l4
የዩጋንዳ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ
የዩጋንዳ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒምስል AP

መንበሩ ዋሽንግተን ዩኤስ አሜሪካ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የምግብ ፖሊሲ ተመራማሪ ተቋምና የዩጋንዳ መንግሥት በጋራ ያዘጋጁት ጉባዔ በግምት ሁለት መቶ ሚልዮን ሕዝብ ባልተመጣጠነ አመጋገብ የሚሰቃይባትን አፍሪቃ የምግብ ምርት ማሳደግ የሚቻልበትን ዘዴ ያፈላልጋል። ሠላሣ አፍሪቃውያት ሀገሮች በሚወከሉበት ዓቢይ ጉባዔ ላይ የዩጋንዳ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒና የሴኔጋል አቻቸው አብዱላዬ ዋድና የሥነ ጽሑፍ የኖቤል ተሸላሚ ናይጀሪያዊው ደራሲ ዎሌ ሾይንካ ዲስኩር ያሰማሉ። የአህጉሩን የምግብ ዋስትና ለማሻሻል አሁኑኑ አንድ ርምጃ ካልተወሰደ ባልተመጣጠነ አመጋገብ የሚጎዱት አፍሪቃውያን ሕፃናት አሀዝ በሚቀጥሉት ሀያ ዓመታት ውስጥ እንደሚጨምር ከሀያ ዘጠኝ ዓመት በፊት የተቋቋመው ዓለም አቀፉ የምግብ ፖሊሲ ተመራማሪ ተቋም አስጠንቅቋል።