1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃዉያን ስደተኞች በፓሪስ

ሰኞ፣ ግንቦት 3 2007

በማዕከላዊ ፓሪስ የሚገኘዉ ላሻፔል የተባለዉ ሥፍራ ለወትሮዉም ቢሆን ድንበር አቋርጠዉ ወደፈረንሳይ ለገቡና ወደፓሪስ እግር ለጣላቸዉ ተሰዳጆች እንደመነኻሪያ የምትቆጠር ናት ትላለች የፓርሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ።

https://p.dw.com/p/1FOEF
Flüchtlinge im Paris la Chapelle
ምስል DW

ሆኖም ግን የሰሞኑ አክራሟ ከወትሮዉ የተለየ መልክ አሰጥቷታል። እንደሃይማኖት ዘገባም ከተማዉን አቋርጦ ከሚሄድ የከተማ ባቡር ድልድይ ሥር የተተለኩት ሰማያዊና አረንጓዴ ትናንሽ ድንኳኖች ለአካባቢዉም ሆነ ለከተማዉ አዲስ ክስተት ሆኗል። በዚህ ስፍራም ቁጥራቸዉ ወደሁለት መቶ የሚጠጉ አብዛኞቹም ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራና ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች ናቸዉ። ከተሰዳጆቹ ዉስጥም ነፍሰጡሮችና በርካታ ሴቶችም ይገኙበታል። ስደተኞቹን ከፈረንሳይ መንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ እስካሁን ባለማግኘታቸዉም እዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጎ አድራጊዎች ሰብዓዊ እርዳታ እያደረጉላቸዉ ነዉ። ተሰዳጆቹን በስፍራዉ ሄዳ ያነጋገረቻቸዉ ሐይማኖት ከፓሪስ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።

Flüchtlinge im Paris la Chapelle
የስደተኞቹ መጠለያ ድንኳኖች በፓሪስ ጎዳናምስል DW

ሐይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ