1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃ፤ የምግብ ችግሯና የፊናንሱ ቀውስ

ዓርብ፣ ጥር 15 2001

የምግብ ዋጋ በዓለም ገበያ ላይ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ እያደገ ነው የመጣው። በአሁኑም ጊዜ ከሰባት አንዱ የዓለም ነዋሪ ለረሃብ የተጋለጠ ነው።

https://p.dw.com/p/Gf3P
የምግብ ዋጋ ንረትና የሕዝብ ቁጣ
የምግብ ዋጋ ንረትና የሕዝብ ቁጣምስል AP
ሆኖም በተለይ በኢንዱስትሪ ልማት የበለጸገውን ዓለም በጠመደው የፊናንስ ቀውስና የኤኮኖሚ ችግር ሳቢያ የታዳጊ አገሮች ሕዝብ መከራ እየተዘነጋ መሄዱ አልቀረም። ጉዳዩ የፊናንሱን ቀውስ ለማሽነፍ የሚደረገው ጥረት አንድ አካል ሆኖ ሊታይ ይገባል፤ የልማት ዕርዳታው መቀነስ ሁሉንም ነው የሚጎዳው የሚል የኤኮኖሚ ባለሙያዎች አስተያየትም አለ።