1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢህአዴግ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የድርድር መድረክ አዘጋጀ

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ጥር 8 2009

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) «ሕጋዊ እዉቅና ካላቸዉ እና ሰላማዊ ትግል ከሚያካሂዱ «ተፎካካር ፓርቲዎች» ጋር ከሰሞኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያያት መዘጋጀቱን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/2VsNe
Karte Äthiopien englisch

EPRDF to Discuss with Oppo. Parties - MP3-Stereo

እንደ ዘገባዉ ኢህአዴግ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ለመደራደር በሚያለያዩ ነጥቦች ላይ ደግሞ ለመከራረክ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል። እስካሁንም የኢፍዴኃግ፣ የቅንጅት፣ የኢዴፓና የኢዴአን ፓርቲዎች በተዘጋጀዉ መድረክ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀታቸዉን ማመልከታቸዉም በዘገባዉ ተጠቅሷል።

የመድረክ ለዴሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፓርቲያቸዉ ለዉይይት ብቻ ሳይሆን «ለቅድመ ድርድር» ለመሳተፍ አጀንዳ እንደያዘ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። የቅድመ ድርድር ነጥቦች እንዳላቸዉ ፕሮፌሰር በየነ ቢናገሩም ዝርዝሩን መግለፅ ለግዜዉ አስፈላጊ አይደለም ነዉ ያሉት።

Professor Beyene Petros derzeitiger Vorsitzender des Oppositionsbündnisses Medrek
ምስል DW

ኢህአዴግ የሚያዘጋጀዉን መድረክ በጥርጣሬ ዓይን የሚመለከቱት አልጠፉም። መድረኩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአገርቱ የፖለቲካ ቀጣይ ጉዞ ተሳትፎ እንዲኖራቸዉ ተፈልጎ ሳይሆን  በአገርቱ ዉስጥ በቅርቡ የተፈጠረዉን የፖለቲካ ቀዉስ ለማስተንፈስ ያለመ  ነዉ ሲሉም ይተቻሉ። ፕሮፌሰር በየነ ግን የምንሳተፈዉ ለዉጤት ነዉ ባይ ናቸዉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባር ፕሮፌሶር የሆኑት ዶክተር ካሳሁን ብርሃኑ መንግሥት ላይ እንዲህ ያለ ትችት እንደሚሰሙ አመልክተዉ፤  የዉይይት መድረኩ የተዘጋጀዉ የፖለቲካ ቀዉሱን ለማስተንፈስ ብሎ መደምደም እንደሚከብድ ይናገራሉ።

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከፓርቲዎች ጋር ዉይይትና ድርድር እናደርጋለን ካሉትና ከመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ዉጭ «በድብዳቤም ሆነ በአካል» በዚህ መድረክ ላይ እንድንሳተፍ አልተነገረንም ያሉት ደግሞ የሰማያዊ ፓርት ሊቀመንበር መሆናቸዉን የሚናገሩት  ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ናቸዉ።

ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ በተፈጠረዉ ዉስጣዊ ችግሩ ምክንያት በሁለት አመራሮች መያዙ ይታወሳል፤ ዶቼ ቬሌ የፓርቲዉ ሕጋዊ ሊቀመንበር መሆናቸዉን የሚገልፁትን በግዜዉ አመራር ላይ ያሉትን ሌላኛዉን ግለሰብ በእጃቸዉ ስልክ ለመግኘት ያደረገዉ ጥረት ለዛሬ አልተሳካም።

ይሁን እንጅ ኢንጅነር ይልቃል ድርድር ከተባለ ከድርጅት ፖለቲካ ዉጭ አሁን በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል መሆን እንዳለበት ያመለክታሉ።

የአገሪቱ ችግር ከገዥዉ ፓርቲ አቅም በላይ ስለሆነ የሌሎችም ተሳትፎ ያስፈልጋል የሚሉት ኢንጅነር ይልቃል «በመሠረቱ መነጋገር ጥሩ ነዉ» ይላሉ። አክለዉም፣

በመንግሥት በኩል የዉይይቱን ወይም የድርድሩን አጀንዳ ዝርዝር ለማገኘት ያደርገነዉ ሙከራ አልተሳካም።

በገዢዉና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ይካሄዳል ስለተባለዉ የዉይይትና ድርድር አስተያየት እንዲሰጡን የፌስቡክ ገጻችንን ተከታዮች ጠይቀን ነበር። አንዳንዶች «ኢህአዴግ ስር ነቀል ለውጥ ለማድረግ አለመዘጋጀቱ አንዱ ማሳያ መኖራቸው ያለ አምስት ዓመት የማይታወቅ ፓርቲዎችን ከያሉበት ያመጣና ለመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ሲያውላቸው መታየቱ ነው» ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ  «ተፎካካሪ ብላችሁ ስማቸውን የዘርዘራችኋቸው ወያኔ ለማታለያ የፈጠራቸው የውሸት ተፎካካሪ ናቸው። ትክክለኛ ተፎካካሪና ተቃዋሚዎቹማ እስር ቤት ናቸው» የሚል አስተያየታቸዉን ጽፈዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ