1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራቅ የገባችበት ቀዉስና የአሜሪካን ድርሻን

ሐሙስ፣ ሰኔ 12 2006

ኢራቅ ዉስጥ የሱኒ ሚሊሺያዎች የሀገሪቱን ሁለተኛ ታላቅ ከተማ ሞሱልን ከያዙና በባግዳድ አካባቢም ጥቃታቸዉን ካጠናከሩ ወዲህ የፕሬዝደንት ኑሪ አልማሊኪ ሺአቶች የሚበዙበት መንግስት ህልዉና አደጋ ላይ መዉደቁ እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1CMDh
US-Außenminister John Kerry mit irakischem Premierminister al Maliki
ምስል Getty Images

ፕሬዝደንት አልማሊኪ ዩናይትድ ስቴትስ ታጣቂዎቹን በአየር እንድትደበድብላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ ከማግኘቱ አስቀድሞ የሰላ ትችት አስከትሎባቸዋል። የተመድ ኢራቅ ዉስጥ የሚታየዉን ጎራ የለየ ዉጊያ የሀገሪቱን ህልዉና የሚፈታተን መሆን አመልክቷል። በሌላ በኩል የጀርመን ፖለቲከኞች ለኢራቅ የወቅቱ ምስቅልቅ አሜሪካ መፍትሄ ልታበጅለት እንደሚገባ እያመለከቱ ነዉ። የአሜሪካ ፖለቲከኞች በአንፃሩ በዚህ ሁኔታ ለአንድ ወገን ድጋፍ ማስጠቱ አስቸጋሪ እንደሆነ ይገልጻሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ የዋሽንግተን ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ