1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራን በትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ ቆረጠች

ሰኞ፣ ሰኔ 22 2012

ኢራን የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተይዘዉ ይቀረቡልኝ ስትል የእስር ማዘዣ ቆረጠች። ኢራን ይህ ርምጃ ለመዉሰድ የወሰነችዉ የአብዮታዊ ዘብ መሪዋ ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ በመገደላቸዉ ነዉ። ኢራን ከጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ ግድያ ጋር ከትራምፕ ሌላ ሌሎች 35 አሜሪካዉያን እጃቸዉ  አለበት ብላ  እንደምታምን ገልጻለች።

https://p.dw.com/p/3eWqz
Irak Qassem Soleimani
ምስል picture-alliance/AP Photo/Office of the Iranian Supreme Leader

ኢራን የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተይዘዉ ይቀረቡልኝ ስትል የእስር ማዘዣ ቆረጠች። ኢራን ይህ ርምጃ ለመዉሰድ የወሰነችዉ በጎርጎረሳዉያኑ 2020 መጀመርያ የአብዮታዊ ዘብ መሪዋ ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ በመገደላቸዉ ነዉ። ኢራን ከጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ ግድያ ጋር ከትራምፕ ሌላ ሌሎች 35 አሜሪካዉያን እጃቸዉ  አለበት ብላ  እንደምታምን ገልጻለች። ፕሬዚዳንት ትራምፕን ጠፍሮ ይዞ በኢራን ፍርድ ቤት ለማቅረብ ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም እንዲረዳትም ኢራን ጠይቃለች።  ይህን ተከትሎ በኢራን የአሜሪካ ልዩ መልክተኛ ቢራን ሆክ ዛሬ ሳዉዲ አረብያ ላይ በሰጡት መግለጫ የኢራን ይህ  ርምጃ « የፕሮፖጋንዳ ጥበቧ » ሲሉ አጣጥለዋል። በኢራን ተወዳጅ የነበሩት የአብዮታዊ ዘብ መሪ  ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ በጎርጎረሳዉያኑ 2020 ዓመት መጀመርያ ወር በኢራቅ ጉብኝት ባግዳድ አዉሮፕላን ጣብያ በአሜሪካ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ድሮን በቦንብ መገደላቸዉ ይታወሳል።    

 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ