1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሬቻ፤ተቃዉሞና ግድያ

ነጋሽ መሐመድ
ሰኞ፣ መስከረም 23 2009

የመንግሥት ባለሰልጣናት በሚቆጣጠሯቸዉ መገናኛ ዘዴዎች እንዳሉት የፀጥታ ሐይላት በተኮሱት ጥይት የተገደለ ሰዉ የለም ።የአይን ምስክሮች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን የመንግስትን መግለጫ ሐሰት ይሉታል።

https://p.dw.com/p/2Qq56
Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

ኢሬቻ፣ ተቃዉሞ እና ግድያ

እንደ እምነት፤ ባሕል፤ ልማድ ወጉ በሰላም የመድረስ ደስታ፤ ምርት የማፈስ ምስጋና፤ አንዱ ከሌላዉ  የመገናኛ ፌስታ በሆነ ነበር።ኢሬቻ።ዘንድሮ ግን ኢትዮጵያ  ደም አፈሰሰችበት።የየዋሕ ንፁሐን ዜጎችዋን በጣሙን የወደፊት ተስፋ ወጣቶችዋን ሕይወት ቀጨችበት።አካል አጎደለችበት።የመንፈሳዊዉን በዓል መልዕክት፤ መንፈሳዊነቱንም አረከሰችበት።ቢሾፍቱ በደም አበላ ታጠበች።በአስከሬን ጎደፈች።እንዴት፤ እና ለምን? ከዚሕ በፊት ብዙ ጊዜ ብዙዎች በብዙ ምክንያት  ልክ እንደኛ ጠይቀዋል።ዛሬም ፤ መልስ እስኪገኝ፤ ምናልባት ወደፊትም እንጠይቃለን። 

የሟች ቁስለኛዉ ቁጥር አወዛጋቢ ነዉ።መንግሥት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች የሟቾቹን ቁጥር 52 ይላሉ።ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች፤ ተቃዋሚዎችና የፖለቲካ አቀንቃኞ ግን ከ175 እስከ 700 ያደርሱታል።ቁጥሩ  ምናልባት በገለልተኛ ወገን እስኪጣራ እንዳወዛገበ ይቀጥላል።ሰዉ የመሞት መገደሉ ምክንያትም እንዳከራከረ ነዉ።

የመንግሥት ባለሰልጣናት በሚቆጣጠሯቸዉ መገናኛ ዘዴዎች እንዳሉት የፀጥታ ሐይላት በተኮሱት ጥይት የተገደለ ሰዉ የለም ።የአይን ምስክሮች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን የመንግስትን መግለጫ ሐሰት ይሉታል።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲ አንድነት መድረክ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር፤ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ እና የፓን አፍሪቃ ምክር ቤቶች አባል አቶ ገብሩ ገብረ ማርያም ኡቱራ የመንግስትን መግለጫ ዉሸት ከሚሉት አንዱ ናቸዉ።

Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

                      

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትሕ (አንድነት) ፓርቲ ባለሥጣንና የፖለቲካ ተንታኝ አስራት አብረሐም ይጠይቃሉ።«ለሠላማዊ ተቃዉሞ ተኩስ መክፈት ለምን አስፈለገ?» እያሉ።የሕግ ፕሮፌሰር እና የሰብአዊ መብት ጉዳይ አጥኚ ዶክተር አወል ቃሲም አሎ የሟቾቹ ቁጥር አምስት መቶ መድረሱን የሚጠቁሙ መረጃዎች እንደደረሳቸዉ አስታዉቀዋል።ይሁንና የሟች ቁስለኞቹን ትክክለኛ ቁጥር፤ የመሞት መቁሰላቸዉ እዉነተኛ ምክንያትም  ለማወቅ ጊዜ ይፈጃል ባይ ናቸዉ።ግን  የሆነዉ ለምን ሆነ?

                               

አቶ አስራትም መንግሥት ሐላፊነቱን አልተዋጣም ባይ ናቸዉ።

                                      

አቶ ገብሩ

             

በዓሉን ለማክበር ቢሾፍቱ የነበረዉም ወጣት ይሕን ያረጋግጣል።

                                   

2009 የአምናዉ ተቃዉሞ ግጭት እና ግድያ፤ ያደረሰዉ ጥፋት የሚያነጋግርበት፤ ግጭት ግድያዉ የከፋ ጥፋት እንዳያደርስ የሚሰጋበት፤ መፍትሔ የሚጠቆምበት ዓመት መስሎ ነበር።

ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ በተለይ ኦሮሚያ መስተዳድር የባለሥልጣናት ሹም ሽር በማድረግ መፍትሔ ያለዉን እርምጃ  መዉሰዱን ያሳወቀበት፤ ተቃዋሚዎች ትክክለኛ መፍትሔ እንዲገኝ የጠየቁ እና የሚጠይቁበት ዓመት መስሎ ነበር።አልሆነም።የትናንቱ ግድያ ጥፋት ዘንድሮም አምና ምናልባትም የከፋ መሆኑ እንጂ ለኢትዮጵያዉያን አሳዛኙ ድቀት።እና እስከ መቼ?

Äthiopien Anti-Regierungs-Protesten
ምስል REUTERS/T. Negeri

                             

ዶክተር አወል

                             

አቶ አስራት።ዶክተር አወልም  እንደሚሉት በሥልጣን ላይ ያለዉ ፓርቲ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ ሁነኛ መፍትሔ ያመጣል ተብሎ የሚታመንበት ጊዜ አልፏል።መንግሥት ለሕዝቡ ጥያቄ የሰጠና የሚሰጠዉ መልስም እንደ ዶክተር አዉል ትንታኔ የሐል እርምጃ ነዉ።

                                 

አቶ አስራትም ተመሳሳይ እምነት አላቸዉ።ይሁንና ያሁኑ ጠብ፤ ግጭት የጎሳ መልክና ባሕሪ እንዳይዝ አንዳድ ተቃዋሚ ወገኖችም እንዲጠነቀቁ፤ የሐገር ሽማግሌዎች፤ የሐይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጣልቃ እንዲገቡም አቶ አስራት ይመክራሉ።ዶክተር አወል አማራጭ ሐይል መኖሩን ያጠያይቃሉ።አቶ ገብሩ ግን አሁንም ይማፀናሉ።እባካችሁ እያሉ-ኢሕአዴግን።

                             

ግጭት ግድያዉን ለማስቆም፤ ወይም ከእስካሁኑ የከፋ ደም መፋሰስ እንዳይከተል ለማስወገድ አቶ አስራትና ዶክተር አዉል እንዳሉት አብነቱ «የሥርዓት ለዉጥ ነዉ»።ለዉጡ ወይም የለዉጡ ሒደት የተፈራዉን ለማስቀረቱ ግን ዋስትና የለም።ዶክተር አዉል እንደሚሉት ግን ባለፈዉ አንድ ዓመት የታዩ ትብብሮች የሩቅም ቢሆን በጎ ተስፋ ሰጪ ናቸዉ።

 የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት የሞቱን ለማሰብ የሰወስት ቀን ብሔራዊ ሐዘን አዉጇል።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ