1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢቦላ፣ የኅመሙ ምልክቶች

ዓርብ፣ የካቲት 13 2007

አብዛኛውን ጊዜ ሰውነት ለኢቦላ ተሐዋሲ ከተጋለጠ በኋላ የበሽታው ምልክቶች ከስምንት እስከ እስር ቀናት ባሉት ጊዜያትም መታየት ይጀምራሉ።

https://p.dw.com/p/1Eej0
Symbolbild Afrika Ebola Fieberthermometer
ምስል Sia Kambou/AFP/Getty Images

ከወባ እና ከኢንፍሉዌንዛ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በዚህ ወቅት የሚታዩት የበሽታው ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦

  • ያልተለመደ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት
  • ማቅለሽለሽ እና ትውከት
  • ተቅማጥ
  • የጉሮሮ ቁስለት
  • ራስ ምታት
  • የጡንቻ ኅመም
  • የጨጓራ ኅመም
  • ዝለት
  • የምግብ ፍላጎት እጦት

እነዚህ ሁሉ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፤ ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ምልክቶች አንዱ አለያም ኹለቱ ብቻም ሊታይባቸው ይችላል። የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች ከታዩ ከአምስት ቀናት በኋላ በሰውነት የመተንፈሻ አካላት ቀዳዳዎች በኩል መድማት ሊከሰት ይችላል። ይኽ መድማት እንደ አፍ፣ አፍንጫ እና የመራቢያ አካላት ባሉ የሰውነት ቀዳዳዎችም ሊከሰት ይችላል።