ኢትዮዽያ የተወሰኑ የሰብል ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዳይቀርቡ የጣለችውን እገዳ አነሳች
ሐሙስ፣ ሐምሌ 8 2002ማስታወቂያ
ኢትዮዽያ የሰብል ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዳይቀርቡ እገዳ የጣለችው ከሦስት ዓመት በፊት ነበር። በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ አማከለ ይማም እንደገለጹት በተለይ በሁለት ምርቶች ላይ እገዳው ተነስቷል። ምክንያቱም የተትረፈረፈ ምርት በመገኘቱ--እንደአቶ አማከለ ገለጻ። ለጊዜው እገዳው የተነሳው ለበቆሎና ለማሽላ ምርቶች ሲሆን በተቀሩት ላይ ግ ይቀጥላል። የዓለም የምግብ ድርጅት የእገዳው መነሳት ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሶ በቀጣይ ከ120 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ከኢትዮዽያ ገበሬዎች እንደሚገዛ አስታውቋል። ኢትዮዽያ ለውጭ ገበያ ምርቷን ለሽያጭ እንደምታቀርብ እየገለጸች ባለችበት በአሁኑ ጊዜ ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰው አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የቅድመ ረሀብ ማስጠንቀቂያ ዓለም ዓቀፍ ኔትወርክ ይፋ አድርጓል።
መሳይ መኮንን
ተክሌ የኋላ