1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና የአፍሪቃ ቀንድ አዲስ አሰላለፍ

እሑድ፣ ጥር 20 2010

ውስጣዊ ግጭት እና ተቃውሞ የሚንጣት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪቃ ቀንድ ባሉ ሃገራት ዘንድ የሚታየው ጂኦ ፖለቲካዊ ለውጥ የዛሬው እንወያይ መሰናዶ ትኩረት ነው። የቀይ ባሕር መስመርን ተከትሎ ከሶማሊያ እስከ ላይ ግብጽ ድረስ የባሕር በር ባላቸውም ኾነ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወደብ አልባ ሃገራት ዘንድ ነው ፈጣን ለውጡ እየተስተዋለ የሚገኘው።

https://p.dw.com/p/2rdoF
Karte Nil Verlauf und Renaissance-Staudamm Englisch

ኢትዮጵያና የአፍሪቃ ቀንድ አዲስ አሰላለፍ

ኢትዮጵያ በቃጣናው ካሉት እንዲሁም ቀይ ባሕርን ተሻግረው ከሚገኙ ሃገራት ጋር የረዥም ዘመን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባሕላዊ እና ማኅበረሰባዊ ግንኙነት ብሎም ትስስር አላት። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የባሕረ-ሠላጤው ሃገራት፦ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ካታር፣ ኩዌት እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በአፍሪቃው ቀንድ ከምጣኔ ሐብታዊ አንስቶ እስከ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ የባሕረ-ሠላጤው ሃገራት ለአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ትኩረት መስጠታቸው ደግሞ በአካባቢው ለውጦችን እያስከተለ ነው። የባሕረ-ሠላጤ ሃገራቱ ወደ አካባቢው ብቅ ማለታቸው በቃጣናው የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚና የባሕል ምኅዳር ላይ ተጽዕኖ በማሳረፍ ላይ ይገኛል። የቀይ ባሕር መስመርን ተከትሎ ከሶማሊያ እስከ ላይ ግብጽ ድረስ የባሕር በር ባላቸውም ሆነ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወደብ አልባ ሃገራት ዘንድ ነው ፈጣን ለውጡ እየተስተዋለ የሚገኘው። በአፍሪቃ ቀንድ ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች ግንባታውም ሆነ ይህ የለውጥ ሒደት ለአካባቢው ሰላም የሚኖረው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንዴት ይታያል? «የአፍሪቃ ቀንድ አዲስ አሰላለፍ እና ኢትዮጵያ» የዛሬው ውይይታችን ትኩረት ነው። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ