1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና የኤኮኖሚ ብቃት ይዞታዋ

ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2005

የዓለም ኤኮኖሚ መድረክ World Economic Forum በቅርቡ የ 2012/13 ዓ-ም ዓለምአቀፍ የኤኮኖሚ ብቃት፤ የምርታማነት ዘገባውን አቅርቧል።

https://p.dw.com/p/184Qd
ምስል dapd

ዘገባው ኢትዮጵያን ከ 143 ሃገራት መካከል በ 121ኛ ቦታ አስቀምጦ ነበር። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ውስጥ ደግሞ ከ 37 ሃገራት መካከል 22ኛውን ቦታ ነው የያዘችው።

ጥናቱ የተጠናቀረው 12 የኤኮኖሚ ዕድገት ምሶሶዎች የተባሉ ዘርፎችን በማጤን ሲሆን ከነዚሁ መካከል መዋቅራዊ ይዞታ፣ የገበያ ብቃት፣ ከፍተኛ ትምሕርት፣ ጤና ጥበቃ፣ የስራ ገበያ ሁኔታ፣ የንግድና የፊናንስ ገበዮች መስፋፋት እንዲሁም ተሃድሶን የመሳሰሉት ይገኙበታል።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ዕቅድ ተቋም UNDP ም በተመሳሳይ ጊዜ Human Development Index በመባል የሚታወቅ የያዝነውን የጎርጎሮሳውያኑን 2013 ዓ-ም የማሕበራዊ ልማት ዘገባውን ማውጣቱ አይዘነጋም። ዘገባው ኢትዮጵያ ከ 187 ሃገራት መካከል በ 173ኛው ቦታ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል።

በጉዳዩ ባለፈው ሣምንት በጀርመን የአፍሪቃ የሰላምና የዕድገት አማካሪ ከሆኑት የኤኮኖሚ ምሁር ከዶር/ፈቃደ በቀለ ጋር ቃለ ምልልስ ማድረጋችን ይታወሳል። ዛሬም በዚሁ የማሕበራዊ ልማትና የኤኮኖሚ ብቃት ጉዳይ በመቀጠል መፍትሄ ጠቋሚ የሆነውን ሁለተኛና ማጠቃለያ ክፍል አቅርበናል፤ ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ