1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና የዓለም የንግድ ድርጅ ት

ሐሙስ፣ መጋቢት 11 2006

ኢትዮጵያ፣ 152 ሃገራትን ያቀፈው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO)አባል ለመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በ 4ኛውና በመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ እንደምትገኝ ተገለጠ። ስለዚህ ድርድር ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

https://p.dw.com/p/1BTRR
ምስል AP Photo

ኢትዮጵያ፣ ከሰሃራ ምድረ በዳ በስተደቡብ ፣ የዓለም ባንክ በሚያቀርበው ዘገባ መሠረት ፈጣን የኤኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ከሚገኙ ሃገራት መካከል አንዷ ናት። አፍሪቃ የወደፊት የንግድ እምብርት በመሆን አያሌ ሃገራትን የሚያማልል ክፍለ ዓለም እንደሚሆን ይታሰባል። ክፍለዓለሙ በጥሬ ሃብት የታደለ ከመሆኑም ሌላ ቀስ በቀስ ኢንዱስትሪዎችንም በማስፋፋት ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ነው። በመሆኑም ከአውሮፓ ለምሳሌ ያህል የጀርመን ኢንዱስትሪዎች በተለይ በደቡብ አፍሪቃ በስፋት ነው የተሠማሩት። ቁጥራቸውም 600 መድረሱ ታውቋል። በአህጉሩ በሰፊው የንግድ ልውውጥ የምታደርገው ቻይና መሆኗ የሚታበል አይደለም።

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የነጻ ገበያውን ንግድ ማስፋፋት እንደሚጠበቅባት የታወቀ ሲሆን የንግድ ባለሥልጣናቱ እንደሚሉት መርኋ በዚሁ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ፤ ሁሉንም ለግሉ የኤኮኖሚ ዘርፍ ማስረከብ አይገባም የሚል አቋም ነው ያላቸው።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ