1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅና ተቃዋሚ ፓርቲ

ዓርብ፣ ሐምሌ 15 2003

የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫዉ እንደሚለዉ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ኢትዮጵያዊ በይፋ ከሚነገረዉ ይበልጣል

https://p.dw.com/p/RbXN
የርዳታ ዕሕልምስል picture alliance/dpa

የኢትዮጵያ መንግሥት ሐገሪቱን በመታዉ ድርቅ ለረሐብ የተጋለጠዉን ሕዝብ ቁጥር አሳንሶታል ሲል አንድ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ወቀሰ።የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫዉ እንደሚለዉ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ኢትዮጵያዊ በይፋ ከሚነገረዉ ይበልጣል።ፓርቲዉ የራበዉን ሕዝብ ከከፋ አደጋ ለማዳን እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት ያስልጋል ብሏልም።የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት የበላይ ሐላፊ በምሥራቅ አፍሪቃ ለረሐብ የተጋለጠዉን ሕዝብ ተዘዋዉረዉ እየጎበኙ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ታደሠ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ