1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዊቷ አክቲቪስት በዳቮሱ ጉባኤ

ሐሙስ፣ ጥር 16 2011

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተሳተፉበት የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ ኢትዮጵያዊቷ አክቲቪስት የትነበርሽ ንጉሴ ተጋብዛለች። የትነበርሽ በዘንድሮው ጉባኤ የተጋበዘችው በማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ ፈጣሪ ከተባሉ 30 ዓለም አቀፍ መሪዎች አንዷ ሆና በመመረጧ ነው።

https://p.dw.com/p/3C8ez
Äthiopien Gewinnerin des alternativen Nobelpreises, Yetnebersh Nigussie
ምስል light for the world

ኢትዮጵያዊቷ አክቲቪስት በዳቮሱ ጉባኤ

የዓለም ግዙፍ ኩባንያዎች ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት እንዲሰጡ የሚወተውት እና "ችሎታን ዋጋ" እንስጥ የተሰኘ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በስዊትዘርላንድ የዳቮስ ከተማ ይጀመራል። በዘመቻው ከ100 በላይ ግዙፍ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ። የ36 አመቷ ኢትዮጵያዊት የሰብዓዊ መብት ጠበቃ እና አራማጅ የትነበርሽ ንጉሴ ጉዳዩን በኃላፊነት ይዘው ከሚሰሩ መካከል አንዷ ነች።

የትነበርሽ ዘመቻው "ችሎታችንን እንጂ አካል ጉዳታችንን አትዩ" የሚል መልዕክት የማስተላለፍ ውጥን እንዳለው ለDW ተናግራለች። ኢትዮጵያዊቱ አራማጅ በዘንድሮው ጉባኤ የተጋበዘችው በማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ ፈጣሪ ከተባሉ 30 ዓለም አቀፍ መሪዎች አንዷ በመመረጧ ነው።

ከየትነበርሽ ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

እሸቴ በቀለ

ተስፋለም ወልደየስ