1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዊቷ የቢግ ብራዘር ተሳታፊ

ዓርብ፣ ኅዳር 15 2004

ከማታውቃቸው ሰዎች ጋር በግዴታ ሳይሆን በውዴታ ለመኖር የፈቀደችው ኢትዮጵያዊት ሀኒ መኩሪያ፤ ለ91 ቀናት በደቡብ አፍሪቃ ቢግ ብራዘር በመባል በሚታወቀው ቤት ቆይታለች።

https://p.dw.com/p/RyIS
የቢግ ብራዘር ቤት በጀርመንምስል Big Brother
24 ሰዓት ሙሉ ፤ የምንበላው፣ የምናወራው፣ የምናደርገው ነገር በቪድዮ እየተቀረፀ ለህዝብ እንዲታይ የምንፈቅድ ስንቾቻችን እንሆን? ነገሩ ቢግ ብራዘር በመባል በአለም ዙሪያ ስለሚቀርበው የቴሌቪዥን ዝግጅት ነው። እስካሁን በ70 አገሮች ይህ ፕሮግራም ሲተላለፍ ከአፍሪቃ ተመሳሳይ ፕሮግራም በማቅረብ ብቸኛዋ አገር ደቡብ አፍሪቃ ነች። ቢግ ብራዘር ለመጀመሪያ ጊዜ እኢአ በ 1999 ዓ ም በኔዘርላንድስ ቴሌቪዥን ለተመልካች ቀረበ። ኃላም በርካታ አገሮች ይህንን አይነት ፕሮግራም በየአገራቸው ማካሄድ ጀመሩ። በ6ኛው ዙር የደቡብ አፍሪቃ ቢግ ብራዘር ውድድር የሌሎችንም የአፍሪቃ ዜጎች ያሳተፈ ሲሆን በዚህም ዝግጅት ላይ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል። ከነሱም ውስጥ አንዷ ሀኒ መኩሪያ ናት። ልደት አበበ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ