1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

ኢትዮጵያውያት ተመራማሪዎች

ረቡዕ፣ የካቲት 4 2012

ከጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓ,ም ጀምሮ የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት በወሰነው መሠረት በሳይንስ ዘርፍ የተሠማሩ አዋቂ እና ወጣት ሴቶች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ይታሰባሉ። ትናንትም ዕለቱ ለስድስተኛ ጊዜ በዓለም ደረጃ  ታስቧል።

https://p.dw.com/p/3XgKr
Frau Wissenschaft Mikroskop Fotolia
ምስል WavebreakmediaMicro/Fotolia

የካቲት ሴት ሳይንቲስቶች የሚታሰቡበት ወር

ከጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓ,ም ጀምሮ የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት በወሰነው መሠረት በሳይንስ ዘርፍ የተሠማሩ አዋቂ እና ወጣት ሴቶች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ይታሰባሉ። ይህ የተደረገበት ዋና ዓላማም ሴቶች በሳይንስ ዘርፍ የሚኖራቸው ተሳትፎ እና ወደምርምሩ የመግባት እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማበራታታት ነው። እስካሁን የተሳካላቸው ጥቂትም ቢሆኑ ሴቶች በየወጡበት ማኅበረሰብ በፆታቸው ምክንያት የሚያጋጥማቸውን ተጽዕኖ ተቋቁመው በተለያዩ የምርምር ዘርፎች መሠማራታቸው አዳጊ ሴቶችን የማነቃቃት ሚና እንዳለው ብዙዎች ያምናሉ። ትናንትም ዕለቱ ለስድስተኛ ጊዜ በዓለም ደረጃ  ታስቧል። የዕለቱ ሳይንስና ቴክኒዎሎጂ መሰናዶ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሴት ተመራማሪዎችን እንግዳው አድርጓል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ሸዋዬ ለገሰ