1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያንም ሰለባ የሆኑበት የደቡብ አፍሪቃ የፖለቲካ አመጽ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 8 2013

ደቡብ አፍሪቃ በፖለቲካ አመጽ ስጥናት ከሳምንት በላይ ሆነ። የአመጹ መነሻ የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ የቀረበባቸውን የሙስና ክስ ለማጣራት የተሰየመው ፍርድ ቤት ችሎት  ባለመቅረባቸው በወሰነው ብይን መታሰራቸው ነው።

https://p.dw.com/p/3wXfD
Südafrika | Ausschreitungen in Durban
ምስል AFP/Getty Images

አመጽ በደቡብ አፍሪቃ

ደቡብ አፍሪቃ በፖለቲካ አመጽ ስጥናት ከሳምንት በላይ ሆነ። የአመጹ መነሻ የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ የቀረበባቸውን የሙስና ክስ ለማጣራት የተሰየመው ፍርድ ቤት ችሎት  ባለመቅረባቸው በወሰነው ብይን መታሰራቸው ነው። በተለይ የትውልድ ስፍራቸው በሆነው ኳዙሉ ናታል የተሰኘው ግዛት በአመጹ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ውድመትና ጉዳት ደርሷል። በሌሎችም ከተሞች ቢሮዎች እና ሱቆች ዝርፊያ እና ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። በዚህ መሀልም እዚያ የሚኖሩ እና በንግድ ዘርፍ የተሠማሩ ኢትዮጵዮውያን ንብረትም መዘረፍ መውደሙን በደርባን ኗሪ የሆኑትና የፍትህ ቢሮ ሠራተኛ  አቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል ገልጸውልናል። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ ስለሁኔታው ጠይቄያቸዋለሁ። የሰሞኑ አመጽ ዛሬ ሰከን ማለቱ ተሰምቷል እና ሁኔታው እንዴት ነው በሚል ላስቀደምኩት ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ይጀምራሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ