1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን ስለ ተሳናባቿ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ምን ይላሉ?

እሑድ፣ መስከረም 16 2014

"ፖለቲካን እንደ ሳይንቲስት ይመለከታሉ" የሚባልላቸው መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው አመታት በተክለ-ስብዕናቸውም ይሁን በአመራር ክህሎታቸው አድናቆትን አትርፈዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኃይለ ማርያም ደሳለለኝና መለስ ዜናዊን ጨምሮ ከበርካታ መሪዎች ጋር ድንበር ለሚሻገሩ ችግሮች መፍትሔ ፍለጋ ተወያይተዋል

https://p.dw.com/p/40sks
Deutschland Afrika-Gipfel bei Bundeskanzlerin Angela Merkel
ምስል picture-alliance/dpa/K. Nietfeld

ኢትዮጵያውያን ስለ ተሳናባቿ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ምን ይላሉ?

"ፖለቲካን እንደ ሳይንቲስት ይመለከታሉ" የሚባልላቸው መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው አስራ ስድስት አመታት በተክለ-ስብዕናቸውም ይሁን በአመራር ክህሎታቸው አድናቆትን አትርፈዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለለኝ እና አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ከበርካታ አገራት መሪዎች ጋር ድንበር ለሚሻገሩ ችግሮች መፍትሔ ፍለጋ ተወያይተዋል።

ከቅርቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የከባቢ አየር ለውጥ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ። የተሻለ ዕድል ፍለጋ ከአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ሰዎች መብዛት ቀውስ ሲፈጥር ለመፍትሔ የጀርመንን በር የከፈቱት አንጌላ ሜርክል ናቸው። ለአፍሪካውያን የሥራ ዕድል የሚፈጥር ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተባለ መርሐ-ግብር ተቀርጾ ተግባራዊ ለማድረግ የተሞከረውም በእርሳቸው የሥልጣን ዘመን ጀርመን የቡድን 20 አገራት ፕሬዝደንት ሳለች ነው። እነዚህ ጉዳዮች አንዳንዶቹ ለኢትዮጵያውያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም የቀረቡ ናቸው። ኢትዮጵያውያን ስለሜርክል ሲጠየቁም በግንባር ቀደምትነት ያነሷቸዋል። 

ስዩም ጌቱ 
እሸቴ በቀለ 
ሒሩት መለሰ