1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞች በሊቢያ ለወራት ታስረው ነበር ተብሏል

ዓርብ፣ ጥር 18 2010

ለወራት በሊቢያ እስር ቤቶች የቆዩ 20 ኢትዮጵያውያን ትላንት ሐሙስ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ በሁለተኛው ዙር የሚመለሱ አርባ አምስት ስደተኞች የጉዞ ሰነድ መውሰዳቸውን እና ከሰሞኑ እንደሚመለሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/2razs
Gambia freiwillige Rückkehrer aus Libyen auf dem Flughafen in Banjul
ምስል Reuters/L. Gnago

ስደተኞች በሊቢያ ለወራት ታስረው ነበር ተብሏል

ሊቢያን በመሸጋገሪያነት ተጠቅመው ወደ አውሮፓ ለመግባት ሞክረው ያልተሳካላቸው ስደተኞች በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ለባርነት ከመሸጥ እስከ እስር ያሉ ስቃዮች እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ስደተኞች መካከል በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር እንግልት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ጀምረዋል፡፡

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከሊቢያ ኢትዮጵያውያን እንዲሚለሱ እርዳታ እያደረገ ያለውን የIOM የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ሰይፈሥላሴን አነጋግሯል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ