1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ኢትዮጵያ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከተጋለጡ ጎራ ተመደበች

ሐሙስ፣ የካቲት 7 2011

ኢትዮጵያ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከተጋለጡ አገራት መካከል እንደምትገኝበት የአውሮጳ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ሽብርተኞች እና ወንጀለኞች ሊጠቀሙባቸው ይቻላሉ ያላቸውን 23 አገራት በትናንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል። ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ቦትስዋና፣ ጋና፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያ እና ቱኒዝያ ከ23ቱ አገራት መካከል ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/3DNqu
Äthiopien Währung Birr
ምስል DW/Eshete Bekele Tekle

23 አገሮች ሽብርተኞች እና ወንጀለኞች ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ ተብሏል

ኢትዮጵያ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከተጋለጡ አገራት መካከል እንደምትገኝበት የአውሮጳ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ሽብርተኞች እና ወንጀለኞች ሊጠቀሙባቸው ይቻላሉ ያላቸውን 23 አገራት በትናንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል። ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ቦትስዋና፣ ጋና፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያ እና ቱኒዝያ ከ23ቱ አገራት መካከል ይገኙበታል። ኢትዮጵያ ከዝርዝሩ የገባችው የባንኮች እና የገንዘብ አሰራራቸው ጉድለት ካለባቸው አገራት አንዷ በመሆኗ ነው። የመን፣ አፍጋኒስታን፣ ኢራን እና ኢራቅም ተመሳሳይ ችግር አለባቸው ተብሏል። 
ኮሚሽኑ የእያንዳንዱን አገር የገንዘብ እና የባንክ አሰራር ያሉበትን ችግሮች፤ ሕጋዊ አሰራሮች እና ሕጋዊ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት የተዘጋጁ አሰራሮች መመርመሩን አስታውቋል። 
ኢትዮጵያን ጨምሮ ችግር አለባቸው የተባሉት 23 አገሮች ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርን በገንዘብ ለመደገፍ የሚደረግ ጥረትን በመከላከል ረገድ ቁልፍ ችግሮች እንዳለባቸው የአውሮጳ ኮሚሽን አስታውቋል።
ገበያው ንጉሴ 
ነጋሽ መሐመድ