1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ መንግሥት ማዘኑን ገለፀ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2008

የዋሽንግተን ዲሲ እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ትናንት ዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ፅሕፈት ቤት አጠገብ ባደረጉት ሠልፍ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንድያሳርፍ ጠይቀዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ ሰበብ ሰዎች መገደላቸዉ እንዳሳዘነዉ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/1JfOh
ምስል Reuters/T. Negeri

[No title]

የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ሐይላት ለተቃዉሞ ሰልፍ አደባባይ የወጡ ሰላማዊ ሰዎችን መግድልና ማቁሰሉን ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አወገዙ።የዋሽንግተን ዲሲ እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ትናንት ዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ፅሕፈት ቤት አጠገብ ባደረጉት ሠልፍ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንድያሳርፍ ጠይቀዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ ሰበብ ሰዎች መገደላቸዉ እንዳሳዘነዉ አስታዉቋል።በአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ክፍል ቃል አቀባይ የኢትዮጵያ መንግስት እና ተቃዋሚዎቹ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ አደራ ብለዋል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ