1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ የናይል ወንዝ ዉዝጋባቸዉን ይፍቱ  

ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2011

በኢትዮጵያ የሕዳሴዉ ግድብ ግንባታ መጀመርን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ የገቡበትን ዉዝግብ ሊፈቱ የሚገባ መሆኑን « ክራይሲስ ግሩፕ» የተባለዉ በግጭቶች ላይ የሚሰራዉ ድርጅት በቅርቡ ይፋ ያደረገዉ ዘገባ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/3FgSZ
Ägypten Kairo Nil-Fluss
ምስል Imago/Zumapress

ግብፅ 90 % የዉኃ ፍላጎትዋን የምታሟላዉ ከናይል ነዉ  

በኢትዮጵያ የሕዳሴዉ ግድብ ግንባታ መጀመርን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ የገቡበትን ዉዝግብ ሊፈቱ የሚገባ መሆኑን « ክራይሲስ ግሩፕ» የተባለዉ በግጭቶች ላይ የሚሰራዉ ድርጅት በቅርቡ ይፋ ያደረገዉ ዘገባ አስታዉቋል። የአባይ ወንዝ ኢትዮጵያን ለቆ ሲወጣ ናይል የሚባል ሲሆን 84 % የሚሆነዉ የናይል ወንዝ ዉኃ የሚፈልቀዉ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ። ግብፅ 90 % የሆነዉን ንፁሕ የዉኃ ፍላጎትዋን የምታሟላዉ ከናይል ወንዝ መሆኑ ይታወቃል።  በዚህም ግብፅ ማንኛዉም በአባይ ወንዝ ላይ የሚዘረጋ የኃይል ማመንጫ የግብፅን ዉኃ ፍሰት እንዳይቀንሰዉ ትሰጋለች። የብራስልሱ ወኪላችን ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን የናይል ዉኃ አጠቃቀምን በተመለከተ « ክራይሲስ ግሩፕ» የተባለዉ በግጭቶች ላይ የሚሰራዉ ድርጅት ምሁርን አነጋግሮ ዘገባ አዘጋጅቶአል። 

አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ