1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ነሐሴ 8 2008

መንግሥት ሰልፎችን ለማስቆም ጠንካራ እርምጃዎች ቢወስድም የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ የሚደረገው ጥሪ እንደቀጠለ ነው ። ይህ ወዴት ያመራል ? ተጨማሪ የሰዎች ህይወት እንዳይጠፋስ ምን መደረግ አለበት ?

https://p.dw.com/p/1JhW9
Äthiopien Protest
ምስል Reuters/T. Negeri

ኢትዮጵያ ፣ተቃውሞውና የመንግሥት እርምጃ

ባለፈው ሳምንት በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች የሰዎች ህይወት መጥፋቱ ሰልፈኞች ለከባድ ድብደባ መዳረጋቸው እና መታሰራቸው አሁንም እያነጋገረ ነው። አጀማመራቸው ሰላማዊ የነበረው እነዚህ ሰልፎች መጨረሻቸው ግድያ ድብደባ እና እሥራት መሆኑ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችንም እያስነሳ ነው ። ሰልፎቹን በውጭ ጠላት ኃይሎች የተደረጀ » የሚለው መንግሥት ሰላማዊ ተቃውሞ ለማካሄድ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ እርምጃ ነው የወሰደው ተብሏል ። ይህን የሚያጣሩ ታዛቢዎችን እንድታስገባ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ኢትዮጵያን ጠይቋል ። መንግሥት ሰልፎችን ለማስቆም ጠንካራ እርምጃዎች ቢወስድም የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ የሚደረገው ጥሪ እንደቀጠለ ነው ። ይህ ወዴት ያመራል ? ተጨማሪ የሰዎች ህይወት እንዳይጠፋስ ምን መደረግ አለበት ? የዛሬው እንወያይ የሚያነሳቸው ነጥቦች ናቸው ።ሙሉውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ተከታተሉ ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ