1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ እና የመልካም አስተዳደር ይዞታ

እሑድ፣ ኅዳር 5 2008

የመልካም አስተዳደር መጓደል በልማት እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ማነቆ ነው። ሕዝብንም የልማት ውጤት ተጠቃሚ እንዳይሆን ያደርጋል፣ በሚል ሕዝብ እና መንግሥት አዘውትረው በቅሬታ ሲናገሩ ይሰማል።

https://p.dw.com/p/1H5Tb
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ኢትዮጵያ እና የመልካም አስተዳደር ይዞታ

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንኑ አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ በየጊዜው የተለያዩ ጥረት ማድረጉ ይሰማል። ይሁን እንጂ፣ ችግሩ እየባሰ እንጂ እየቀነሰ እንዳልሄደ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ከፓብሊክ ሰርቢስ እና የሰው ኃይል ሚኒስቴር ጋር ባንድነት ያዘጋጀው እና ከጥቂት ጊዜ በፊት በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት መካከል ምክክር የተካሄደበት የመልካም አስተዳደር ጥናት አሳይቶዋል። ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? መፍትሄውስ ምን መሆን አለበት? በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሂደናል።

አርያም ተክሌ

እሸቴ በቀለ