ኢትዮጵያ እና የድህነት ቅነሳው ሂደት
ሰኞ፣ የካቲት 2 2007ማስታወቂያ
እና ወደ ድህነት አዘቅትየመውደቅ ስጋት እንደተደቀነበት የባንኩ ዘገባ ገልጾዋል። የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር አሰናዳሁት ባለው እና ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባወጣው የቅርብ ጊዜ ዘገባው መሠረት በኢትዮጵያ የድህነት መጠን ቀንሶ በ2003 እና 2004 ዓም 30 ከመቶ መድረሱን ገልጧል። ሆኖም የዓለም ባንክ በዚሁ ዘገባው በኢትዮጵያ 37 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ እንደሚገኝ እና ወደ ድህነት አዘቅት የመውደቅ ስጋት እንደተደቀነበትም አስታውቋል። ባንኩ ባወጣው ዘገባ፣ ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት እያሳየች ነው ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ድሀ የነበሩ ሰዎች ይበልጥ መደኽየታቸውንም አስገንዝቧል። የዓለም ባንክ ስላወጣው የድህነት ቅነሳ ዘገባ ውይይት አካሂደናል።
አርያም ተክሌ
ማንተጋፍቶት ስለሺ