1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የልማት ተምሳሌ የመሆን እድል አላት መባሉ

ዓርብ፣ መጋቢት 20 2011

ኢትዮጵያ አፋጣኝ የልማት ተግባራዊ እርምጃዎችን መተግበር ከቻለች የአፍሪካ የልማት ተምሳሌት መሆን የሚያስችል እድል ያላት መሆኑን የሚያሳይ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡ ከርሃብ ምድር ወደ ተስፋ ምድር በሚል በበርሊን የህዝብ እና የልማት ተቋም የተከናወነው ጥናቱ ኢትዮጵያ በትምህርት ፡ በጤና ፡ በወሊድ ምጣኔ ቅነሳ እና መልካም ስራ ማከናወኗን አትቷል፡፡

https://p.dw.com/p/3Fu1R
Karte Sodo Ethiopia ENG

የኢትዮጵያ የልማት ተምሳሌ የመሆን ዕድል

 

ኢትዮጵያ አፋጣኝ የልማት ተግባራዊ እርምጃዎችን መተግበር ከቻለች የአፍሪካ የልማት ተምሳሌት መሆን የሚያስችል እድል ያላት መሆኑን የሚያሳይ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡ ከርሃብ ምድር ወደ ተስፋ ምድር በሚል በበርሊን የህዝብ እና የልማት ተቋም የተከናወነው ጥናቱ ኢትዮጵያ በትምህርት ፡ በጤና ፡ በወሊድ ምጣኔ ቅነሳ እና መልካም ስራ ማከናወኗን አትቷል፡፡ በሃገሪቱ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በአማካኝ የወሊድ ምጣነው አንድ እናት ትወልድ ከነበረው ሰባት ልጅ ወደ አራት መውረዱ የልማት ስራዎችን ከህዝብ ቁጥሩ ጋር አጣጥሞ ለማስኬድ ትልቅ እድል ነው ተብሏል፡፡

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ